ታሪክ ታሪክ

ዘመነ መሳፍንት

 

አፄ ቴዎድሮስ በአንበሶች ተከበው

 

 

 

ከ1755 እስከ 1855 እ.ኤ.አ. ኢትዮጵያ እንደገና ከአለም ጉዳዮች ተገላ ነበር። ይህ ጊዜ «ዘመነ መሳፍንት» ይባላል ምክኒያቱም

የኢትዮጵያ ንጉሠ ነገሥቶች በራስ ሚካኬል ስሁል፣ ራስ ወልደ ሥላሴ፣ ራስ ጉግሳ እና በመሳሰሉት ቁጥጥር ስር ነበሩ።

ራስ ጉግሳ በ17ኛው ክፍለ ዘመን ጎንደርን በመምራታቸው የቤተ መንግሥቱን ቋንቋ ከአማርኛ ወደ ኦሮምኛ ለውጠው ነበር።

የኢትዮጵያ ግለልኘነት ያበቃው ከእንግሊዝ ጋር ግንኙነት ስትጀምር ነው። ኢትዮጵያ እንደገና የተዋሀደችው እንዲሁም

የዘውዱ ስልጣን የተጠናከረው በ1855 እ.ኤ.አ. በአፄ ቴዎድሮስ ምክኒያት ነው። የሰሜን አሮሞዎችና ትግሬዎች አመፅና የግብፆች

ተደጋጋሚ ድንበር መጣስ የአፄ ቴዎድሮስ ስልጣን እንዲዳከም አደረጉት። በመጨረሻም ከእንግሊዝ ጋር በነበረው ጦርነት እስረኛ

አልሆንም ብለው አፄ ቴዎድሮስ እራሳቸውን አጠፉ። በ1868 እ.ኤ.አ. ኢትዮጵያና ግብፅ ጉራ በሚባለው ቦታ ተዋጉ።

በአፄ ዮሐንስ አራተኛ የተመሩት የሰሜን ኢትዮጵያ ሀይሎች ድል ተቀናጁ።

በ1889 እና በ1890ዎቹ እ.ኤ.አ. መጀመሪያ፣ የሸዋ ንጉሥ ሳህለ ሥላሴ ከዚያም ዳግማዊ አፄምኒልክ በራስ ጎበና እርዳታ አማካኝነት

ሀገሯን ወደ ደቡብና ምሥራቅ ማስፋፋት ጀመሩ። ከአህመድ ግራኝ ወረራ በኋላ በኢትዮጵያ ቁጥጥር ስር ያልነበሩ፣ ሌሎች ደግሞ

በማንኛው ጊዜ በኢትዮጵይ ቁጥጥር ስር ያልነበሩ ቦታዎች በዳግማዊ አፄ ምኒልክ አገዛዝ ጊዜ በኢትዮጵያ ስር ሆኑ።

ከዚህ ጊዜ በኋላ የኢትዮጵያ ድንበር ብዙ አልተለወጠም። ከ1888 እስከ 1892 እ.ኤ.አ. ድረስ የነበረው የሰፋ ድርቅ ከኢትዮጵያ

ህዝብ በአንድ ሶስተኛ የሚገመተውን ቀጥፎአል።

 

የአውሮፓ ሽሚያ ለአፍሪካ

በ1880ዎቹ እ.ኤ.አ. የአውሮፓ መንግሥቶች በበርሊን ጉባኤ ተስማምተው አፍሪካን በቅኝ ገዢነት መከፋፈል ጀመሩ።

በኢትዮጵያ እና ጣልያን መካከል የነበሩ የዚያ ዘመን ውዝግቦች ወደ አድዋ ጦርነት በ1888 ዓ.ም. አመሩ። በጦርነቱ የጣልያን

ትልቅ ዘመናዊ ጦር በኢትዮጵያ ጦር ትልቅ ሽንፈት የደረሰበት መሆኑ ዓለምን አስደነቀ።

Pages: 1  2  3  

የመንግስት ኮሙዩኒኬሽን ጉዳዮች ጽ/ቤት
ፖ ሳ ቁጥር: 1364/530
ስልክ ቁጥር: +251-115-52-81-13
:+251-115-52-81-92
ፋክስ : +251-115-52-20-60
: +251-115-54-25-87
Follow Us
Facebook
google +
youtube
twitter
© 2016 የኢፌድሪ መንግስት ኮሙዩኒኬሽን ጉዳዮች ጽ/ቤት