ታሪክ ታሪክ

ታሪክ

ቅድመ ታሪክ

ኢትዮጵያ ከጥንት ጀምሮ የሰው ልጅ ከነበረባችው ቦታዎች አንዷ መሆኗ ትታወቃለች። የሰው ፍልሰት ጥናቶች፣ የቅሪተ አካል ጥናቶችና ሌሎች የሳይንሳዊ ዘዴዎች ይህን ያረጋግጣሉ። ድንቅነሽ የምትባለው በአፋር ክልል ውስጥ የተገኘችው አጽም በአለም በዕድሜ ሁለተኛ ጥንታዊ ናት። ከ3.2 ሚሊዮን ዓመታት በፊት በኢትዮጵያ እንደኖረች ይገመታል። ሌሎችም ታዋቂ አጽሞች በኢትዮጵያ ተገኝተዋል።

የመጀመሪያዎቹ መንግስታት

በ፰፻ ዓመተ ዓለም አካባቢ ደአማት የሚባል መንግስት በሰሜን ኢትዮጵያና ኤርትራ ተቋቋመ። በሰሜን ኢትዮጵያ የምትገኘው የሀ የደአማት ዋና ከተማ ነበረች። በየመን የሚኖሩት ሳባውያን በደአማት ላይ ተፅዕኖ እንደነበራቸው የሚታመን ሲሆን ይህ ተፅዕኖ ምን ያህል እንደሆነ ግን በእርግጥ አይታወቅም። ወደ ፬፻ ዓመተ ዓለም አካባቢ የደአማት መንግስት ከስልጣን ሲወድቅ በትናንሽ መንግስቶች ተተካ። ከነዚህ ትናንሽ መንግስቶች አንዱ አክሱም ሲሆን አካባቢውን እንደገና በአንድነት ለመግዛት ችሎ ነበር።

የአክሱማውያን ስፈን በኢትዮጵያ የመጀመሪያው ጠንካራ መንግሥታዊ ማኅበረሰብ ነበር። በፋርስ፣ ሮማ እና ቻይና ይገኙ ከነበሩ ታላላቅ መንግሥታት በወደረኛነት የሚቆጠር ትልቅ ኅይል ነበር። በ4ኛው ምእተ ዓመት አክሱም ወደ ክርስትና ተለወጠ። በ6ኛው ምእት ዓመት የአክሱማውያን ግዛታዊ ቁጥጥር የዛሬዋን የመን ግዛት ይጨምር ነበር። ግን በ7ኛው እና በ፰ኛው አምኣት የአክሱም ሥልጣኔ በእስልምና መነሣት እና መስፋፋት ተዳክሞ ለውድቀት በቃ። ተከታዩ የዛጔ ሥርወ-መንግሥት ልክ በድንገት እንደተነሳ በድንገት ሲያበቃ፣ ይኵኖ አምላክ ሥልጣን በ ፲፪፻፷፪ ዓ.ም. ጨበጡ፤ እንዲያም ሲል የሰለሞናዊው ሥርወ-መንግሥትን መለሱ።

ከአውሮፓ ጋር የታደሰ ግንኙነት

የንጉሠ ነገሥት ፋሲለደስ ቤተ መንግሥት

በ፲፭ኛው ምዕተ ዓመት መጀመሪያ ኢትዮጵያ ከአክሱም ጊዜ በኋላ ለመጀመሪያ ጊዜ ከአውሮፓ ጋር ግንኙነት ጀመረች።

ከእንግሊዝ ንጉሥ ሄነሪ አራተኛ ወደ የአቢሲኒያ ንጉሠ ነገሥት የተላከ ደብዳቤ እስከ ዛሬ ድረስ አለ። በ1428 እ.ኤ.አ.

አፄ ይስሐቅ ወደ የአራጎን ንጉሥ አልፎንዞ አምስተኛ ሁለት መልክተኞች ልከው ነበር። ግን የመጀመራያው

ያልተኳረጠ ግንኙነት በአፄ ልብነ ድንግል ስር ከፖርቱጋል ጋር ከ1508 እ.ኤ.አ. ጀምሮ ነው የተካሄደው።

ኢትዮጵያ በአህመድ ግራኝ ስትጠካ፣ ፖርቱጋል አራት መቶ ወታደሮችና የጦር መሳሪያ በመላክ ኢትዮጵያን ረድታለች።

አፄ ሱስንዮስ በፖርቱጋልና እስፓንያ ተጽዕኖ እና ተጨማሪ እርዳታ ከመፈለጋቸው የተነሳ ወደ የሮማ ካቶሊክ ክርስትና ተለወጡ፤

የኢትዮጵያ ይፋ ሀይማኖትንም አደረገቱት። ይህ ውሳኔ ወደ ግዙፍ ተቃውሞና ጦርነት አመራ። በብዙ ሺህ የሚቆጠሩ ሰዎች

ከሞቱ በኋላ፣ የአፄ ሱስንዮስ ልጅ አፄ ፋሲለደስ በ1632 እ.ኤ.አ. ኢትዮጵያ ወደ አርቶዶክስ ክርስትና መመለሷን አወጁ።

አውሮፓውያኖቹንም ከኢትዮጵያ አስወጡ።

Pages: 1  2  3  

የመንግስት ኮሙዩኒኬሽን ጉዳዮች ጽ/ቤት
ፖ ሳ ቁጥር: 1364/530
ስልክ ቁጥር: +251-115-52-81-13
:+251-115-52-81-92
ፋክስ : +251-115-52-20-60
: +251-115-54-25-87
Follow Us
Facebook
google +
youtube
twitter
© 2016 የኢፌድሪ መንግስት ኮሙዩኒኬሽን ጉዳዮች ጽ/ቤት