ዜና ዜና

9ኛው የኦህዴድ ድርጅታዊ ጉባኤ በጅማ ከተማ በደማቅ ስነ ስርዓት ተጀመረ።


 

ኦህዴድ በዚህ ጉባኤው በርካታ ድርጅታዊ ውሳኔዎችን እንደሚያልፍ ድርጅቱ ትላንት በሰጠው መግለጫ አመልክቷል፡፡

የድርጅቱ ያቀረባቸው ረቂቅ የስያሜ፣አርማና መዝሙር ለውጥ ላይ ተወያይቶ ያፀድቃል ተብሎ ይጠበቃል፡፡

የኦህዴድ ሊቀምንበር ዶ/ር ዐቢይ አህመድና ምክትል ሊቀምንበር አቶ ለማ መገርሳም በመክፈቻ ስነ ስርዓቱ ላይ ታድመዋል፡፡

በመክፈቻ ስነ ስርዓቱ ላይ ንግግር ያደረጉት የኦህዴድ ምክትል ሊቀመንበርና የኦሮሚያ ክልል ፕሬዝዳንት አቶ ለማ መገርሳ ኦህደድ እስካሁን ስህተቶችን ቢፈፅምም፣ ስህተቱን ለማረም እየሰራ መሆኑን ተናግረዋል፡፡

ለክልሉ ሰላምና ለኢትዮጵያ እድገት የድርጅቱ አባላት እጅ ለእጅ ተያይዘው እንደሚሰሩም አመልክተዋል፡፡

የኦህዴድ እና የኢህአዴግ ሊቀመንበር እንዲሁም የኢትዮጵያ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር ዐቢይ አህመድ በበኩላቸው የኢትዮያን አንድነት ለማስጠበቅ ኦሮሞ ኃላፈዲነት አለበት ብለዋል፡፡ "ኦሮሞ አገር መምራት አይችልም የሚሉን አሉ፤ ኦሮሞ አገር መምራት ብቻ ሳይሆን አገር መገንባት ይችላል፤ ኦሮሞ ገዳን ለዓለም እንደ ሰጠ ሁሉ፣ ኦሮሞ በቅርቡ አዲስ ፍልስፍና ለኢትዮጵያና ለአፍሪካ ሰጥቶ ሊያሳያቸው ይፈልጋል" ብለዋል፡፡

በኦሮሞ ስም መነገድ እንደማይቻልና ህግ የማስከበር ኃለፊነቱን ድርጅቱ እንደሚወጣም ዶ/ር ዐቢይ ተናግረዋል፡፡
በጉባኤው ላይ የኦህዴድ እህት እና አጋር ድርጅቶችም በተወካዮቻቸው በኩል ተካፋይ ናቸው፡፡

ተወካዮቹ በአገሪቱ እየመጣ ያለውን ለውጥ ከኦህዴድ ጋር ሆነው ዳር እንዲደርስ የበኩላውቸውን ድጋፍ እንደሚያደርጉም ተናግረዋል፡፡

መስከረም 9/2011