ዜና ዜና

80 በመቶ የሚሆነውን አርሶ አደር ተጠቃሚ ለማድረግ የአግሮ ኢንዱስትሪ ዘርፉን ማጠናከር ይገባል ተባለ።

ሁለተኛው አለም አቀፍ የአግሮ ኢንዱስትሪ ኢንቨስትመንት ፎርም ትናንት በአዲስ አበባ ተከፍቷል።

በመክፈቻ ስነስርዓቱ ላይ ተገኝተው ንግግር ያደረጉት የኢፌዴሪ ፕሬዚዳንት ዶ/ር ሙላቱ ተሾመ 80 በመቶ የሚሆነውን አርሶ አደር ተጠቃሚ ለማድረግ የአግሮ ኢንዱስትሪ ዘርፉን ማጠናከር ይገባል ብለዋል።

መንግስት ዘርፉን ለማጠናከር በርካታ ስራዎችን እየሰራ እንደሚገኝ የጠቆሙት ዶ/ር ሙላቱ መሰል ፎረሞች መካሄዳቸው በዘርፉ የተሻለ ውጤት ለማስመዝገብ ሚናቸው የጎላ ነው ብለዋል።

የኢንዱስትሪ ሚኒስቴር ከተባበሩት መንግስታት ድርጅት የኢንዱስትሪ ልማት ድርጅት /UNIDO/ ጋር በመሆን ያዘጋጁት ሁለተኛው አለም አቀፍ የአግሮ ኢንዱስትሪ ኢንቨስትመንት ፎረም ላይ ከ3ሺህ በላይ ተሳታፊዎች ይኖሩታል የተባለ ሲሆን ፎረሙ ከየካቲት 26-28 በሚሊኒየም አዳራሽ እየተካሄደ ይገኛል፡፡

በፎረሙ ከመላው አለም የተጋበዙ በግብርና ኢንዱስትሪ ኢንቨስትመንት ላይ የተሰማሩ ባለሀብቶች፣ የአለም አቀፍ የገንዘብ ተቋማት፣ አምባሳደሮች፣ የሀገራት መንግስት ተወካዮችና አለም አቀፍ የዘርፉ ድርጅቶች እየተሳተፉ ነው።

የካቲት 27/2010 የኢፌዴሪ መ/ኮ/ጉ/ጽ/ቤት