ዜና ዜና

8ኛው የአርሶና አርብቶ አደር በዓል በአዳማ ከተማ ተከበረ

በ8ኛው የአርሶና አርብቶ አደር በዓል ላይ በግብርናው ዘርፍ የተሻለ አፈፃፀም ያስመዘገቡ ከ550 በላይ ተሳታፊዎች የእውቅናና የማበረታቻ ሽልማት ከኢ.ፌ.ዲ.ሪ ጠቅላይ ሚንስትር አቶ ሀይለማሪያም ደሳለኝ እጅ ተቀበሉ፡፡

የተሳታፊዎች ሽልማት በዘርፉ ብለጫ ያስመዘገቡ አርሶና አርብቶ አደር ከማበረታታትና እውቅና ከመስጠት ባለፈ በአርሶና አርብቶ አደሮች መካከል መመማር ና ጤናማ ውድድር በፍጠር የዘርፉን ውጤት ወደ ላቀ ደረጃ ለማሸጋገር የሚኖረው አስተዋጽኦ ከፍ ያለ እንደሆነ ተመላክቷል፡፡

በ8ኛው የአገር አቀፍ የእርሶ/አርብቶ አደር  ቀን ከተሸለሙ 550 ተሸላሚዎች መካከል  1ኛ ደረጃ እስከ 3ኛ ደረጃ  ባስመዘገቡትና በአከናዎኑት ተግባራት  መሰረት ውጤት ተሰጥተዋል፡፡

በዕለቱ የአንደኛ ደረጃ ተሸላሚዎች ከደበብ ክልል 21 ሚሊን ብር በላይ፣ ከአሮማያ ክልል 19.2 ሚሊዮን ብር በላይ  አማራ ክልል 15.1 ሚሊዮን ብር ፣ ከትግራይ ክልል 8.1 ሚሊዮን ብር በላይ፣ ከቤኒሻንጉል ክልል 10.4 ሚሊዮን ብር፣ ከሀረሬ ክልል 10.1 ሚሊዮን ብር  ካፒታል  ያስመዘገቡ አርሶ አደሮች የዘመናዊ የትራክተር ቁልፍ ከጠቅላይ ሚንስትር ሀይለማሪያም ደሳለኝ እጅ ከሜዳሊያ ጋር ተቀብለዋል፡፡

በዚሁ ውድድር በደቡብ ክልል ጋሞ ጎፋ ዞን ነዋሪ  የሆኑት ወ/ሮ አማረች ለቢኔ  ከሴት ተሸላሚዎች  7.7 ሚሊዮን ብር ካፒታል በማስመዝገብ በ1ኛ ደረጃ ማረግ የዘመናዊ ትራክተር ልዩ ክብር ተሻላሚ  ሆነዋል፡፡ 

በ2ኛ ደረጃ ለሽልማት የበቁ ተወዳዳሪዎች በሰው ሀይል በቀላሉ የሚንቀሳቀስ ትራክተር ተሸልመዋል፡፡ ከአሮማያ ክልል 18.7 ሚሊዮን ፣ ከአማራ ክልል 14.6 ሚሊዮን፣ ከደቡብ ክልል 19.1 ሚሊዮን፣ ከትግራይ 7.7 ሚሊዮን፣ ከጋንቤላ 2.9 ሚሊን፣ ከቤንሻንጉል ክልል 9.6 ሚሊዮ ካፒታል ከሀረሬ 7.8 ሚሊዬን ብር ካፒታል ያስመዘገቡ ባለሀብቶች ለደረጃው የተቀመጠውን ሽልማት አግኝተዋል፡፡

በተመሳሳይ መልኩ የ3ኛ ደረጃ ተሸላሚዎች በሞተር የሚሰራ የውሀ ፓምፕና መዳሊያ ያገኙ ሲሆን  ከኦሮማያ ክልል ከ16.2 ሚሊዮን  በላይ፣ ከአማራ ክልል 10.5 ሚሊዮን በላይ፣ ከደቡብ ክልል 18.4 ሚሊዮን በላይ ፣ ከትግራይ ክልል 7.5 ሚሊዮን በላይ፣ ከቤንሻንጉል ጉምዝ ክልል ከ6.7 ሚሊን ብር በላይ  ካፒታል ያስመዘገቡ ባለሀብቶች የእድሉ ተጠቃሚ ሆነዋል፡፡

በተጨማሪ ለዘርፉ ውጤት መሳካት የተሻለ ድጋፍና ክትትል ያደረጉ የህብረት ስራ ማህበራት፣ ብድርና ቁጠባ ተቋማት፣ የግብርና ልማት ጣቢያ ሰራተኞች፣ የግብርና ተመራማሪዎች፣ የ1ለ5 ቡድኖችና ሌሎች የዘርፉ አጋር አካለት በእየደረጃው ለሽልማት በቅተዋል፡፡

የኢ.ፌ.ዲ.ሪ ጠቅላይ ሚንስትር አቶ ሀይለማሪያም ደሳለኝ በሽልማትና የአውቅና ስነስርዓቱ ላይ ተገኝተው እንደተናገሩት ባለፉት ተከታታይ  15 ዓመታት ግብርናው  በአማካየይ የ8 በመቶ እድገት  ምጣኔ  አስመዝግቧል፡፡ ግብርናው ከ1993 እስከ 2002 ዓ.ም በነበሩት 10 የተሀድሶ አመታት ውስጥ በአማካይ 9 በመቶ በማደግ ለአጠቃላይ የኢኮኖሚው እድገት  ትልቁን ድርሻ ተዎጥቷል፡፡

የመጀመሪያው እድገትና ትራንስፎርሜሽን እቅድ አፈፃፀም  በዋና ዋና የምግብ ሰብሎች በእቅዱ መነሻ  ዘመን የነበረውን  191 ሚሊዮን ኩንታል ምርት  በእቅድ ዘመኑ መጨረሻ 270 ሚሊዮን ኩንታል ማድረግ ተችሏል፡፡  ከዚህም ምርት ውስጥ 95 በመቶ ያህሉ ምርት በገበሬው አነስተኛ መሳ ላይ የተመረተ ነው፡፡

እንደ ጠ/ሚንስቴር አቶ ሀይለማሪያም ገለፃ ዘመናዊ ቴክኖሎጅዎችንና አዳዲስ አሰራሮችን  በአነስተኛ የአርሶ አደር መሳሪያዎች ላይ ተግባራዊ በማድረግ  የግብርና ምርትና ምርታማነትን በማሳደግ  አገሪቷ የተከተለችውን የፖሊሲ አቅጣጫ ውጤታማነት በተግባር ተረጋግጧል፡፡

በመጀመሪያው እድገትና ትራንስፎርሜሽን እቅድ በተፈጥሮ ሀብት ስራ  በእቅድ ዘመኑ  መጀመሪያ የነበረውን 3ነጥብ7 ሚሊዮን ሄክታር   በተለያዩ የተፋሰስ ስራዎች የተሸፈኑ ማሳዎች ከ8 ሚሊዮን ሄክታር በላይ ደርሷል፡፡ ከነዚህ ስኬቶች ጀርባ ያለው ሚስጢር  የህብረተሰቡ ሰፊ የተደራጀ ተሳትፎ ና የመላው አርሶ አደር ርብርብ ነው፡፡

የተፋሰስ ልማት ስራዎችን በመንተራስ  የእንሰሳት መኖ አቅርቦት በመሻሻሉ  በእንስሳት ማድለብና ማሞከት ስራዎች ፣ በንብ ማነብና በሌሎች እንሰሳት ተዋጽኦ ስራዎች  በሚሊዮን ለሚቆጠሩ የገጠር ነዋሪ ወጣቶችና ሴቶች  የአስራ እድል ለመፍጠር ጥረት ተደርጓል፡፡ ለቀጣይ ስራዎች ተሞክሮ የሚሆን ልምድም ተገኝቷል፡፡

በተለይም በግብርናና በተፈጥሮ ሀብት ስራ በአነስተኛ የገበሬዎች ማሳ ላይ የተመሰረተ የእድገት አቅጣጫ  ውጤት መጥቷል፡፡ በዚህ እረገድ አገሪቱ በመጀመሪያ ካፒታል የማከመቸት ምእራፍ እድትገባ አድርጓል፡፡ ይህ የመጀመሪያው ደረጃ የካፒታል ክምችት  ለኢንዱስትሪ ግንባታ የሚጠበቀውን የመንግስት የካፒታል ክምችት ብቃት የሚፈጠርበት ምእራፍ ነው፡፡

አያይዘውም ከገጠር ባህላዊ የእርሻ ተግባር ወደ ሳይንሳዊ አሰራርና የማኑፋክቸሪንግ ዘርፍ ለማሸጋገርና ለዚሁ ተግባር የተዘጋጀ መጠነ ሰፊ የሰው ሀይል  ለማቅረብ የሚቻልበት ደረጃ ላይም ተደርሷል፡፡ የአንድ አገር የግብርና እድገት በሚያሳይበት ወቅት የካፒታል ክምችትና በማኑፋክቸሪንግ ዘርፍ ተቀጥሮ የሚሰራ  የሰለጠነ የሰው ሀይል ማቅረብ  ይጠበቃል፡፡

ይህን መልካም ጅምር መነሻ በማድረግ በዘመናዊ መልኩ ለለዜጎች የስራ እድል ለመፍጠር  መንግስት ስትራቴጅዎችን በመቅረፅ ወደ ተግባር እንቅስቃሴ ተገብቷል፡፡ ዘመናዊ የወጣቶች የግብርና ልማት ተሳትፎ በአግባቡ ከተመራ  የግብርናውን ዘርፍ በማዘመን  ታሪካዊ ተልኮውን ይፈፅማል ብለዋል፡፡       

በ50 አመታት ታሪክ ታይቶ በማይታወቅ ደረጃ  አገሪቷን የገጠማት የድርቅ አደጋ በአገር ውስጥ አቅም  በመንግስትና ህዝብ በጋራ መቋቋም ተችሏል፡፡ ይህ ውጤት የተገኘው ተፈጥሮ መልሶ እንዲያገግም አስቀድሞ የተሰራው ስራ ቱርፋት ነው፡፡  በድርቁ አጋጣሚ  የሰብል ምርት ውጤት በቀነሰባቸው አካባዎች የቀነሰውን የምርት መጠን  ለማካካስ  በበልግ ወቅት በተሰራው የእርሻ  ስራ እና በመስኖ ስራ  ለማካካስ ጥረት ተደርጓል፣ ውጤትም ተገኝቷል ሲሉ  ጠቅላይ ሚንስትር አቶ ሀይለማሪያም አስረድተዋል፡፡

በአገሪቱ ከሚገኙ 14 ሚሊዮን አርሶ አደሮች መካከል  22  በመቶ ያህል ሞዴል አርሶ አደሮችን  ማፍራት ተችሏል፡፡ እነዚህ ሞዴል አርሶ አደሮች  በማህበራትም ይሁን  በተናጠል በእርሻና እርሻ  ተዋጽኦ ማቀነባበሪያ ኢንዱስትሪዎችና የካፒታል ክምችትና የስራ እድል በመፍጠር የየድርሻቸውን እንዲወጡ ጥሪያቸውን  አስተላፈዋል፡፡

አዳማ መጋቢት 3 / 2009