ዜና ዜና

3ኛው የምግብ እና መጠጥ አውደ ርዕይ ተከፈተ፡፡

 የምግብ መጠጥና ፍርማሲዮቲካል ኢንስቲትዩት ከኤስ ፒ ከተባለ ድርጅት ጋር በመተባበር ያዘጋጁት አውደ ርዕይ ዛሬ በኤግዚቪሽን ማዕከል  በይፋ ተከፍቷል፡፡

አውደ ርዕዩን በይፋ የከፈቱት  የኢንዱስትሪ ሚንስትር ዴኤታ በሆኑት ዶ/ር መብራሀቱ መለስ ሲሆን አውደ ርዕይው  ከ13-17/2009 ዓ.ም  እንደሚቆይም ለማወቅ ተችሏል  ፡፡

ዶ/ር መብራሀቱ   አውደ ርይው ሲከፍቱ እንደተናገሩት  ይህ "ጥራት ለአለማአቀፍ ተወዳዳሪነት" በሚል መሪ ቃል የሚደረገው አውደ ርዕይ የምርት መጠንን በማሳደግ አማራቾች  በጥራት በዋጋ ተወዳዳሪ ሆነው ምርቶቻቸውን ለሀገር ውስጥና ለውጭ  ሀገር ገበያ  ለማቅረብ የሚያስችል የገበያ ትስስር መፍጠር ነዉ ብለዋል፡፡

  በአምራች ኩባንያዎችና በአቅራቢዎች መካከል የገበያ ትስስር በመፍጠር ተደራሽነትን  በማሳደግ በአለማቀፍ ደረጃ በምግብና በመጠጥ ኢንዱስትሪ ተወዳዳሪ ለማድረግ  አላማ አለው ብለዋል፡፡

የምግብ መጠጥና ፋርማሲዮቲካል  ኢንስቲትዩት አስተባባሪ የሆኑት አቶ ሰለሞን ታደለ በበኩላቸው" ይህ ኤግዚቪሽን የሚካሄደው አምራቹንና  ገዢዎችን  በማስተሳሰር እንዲሁም የተለያዩ ልምድ ለውውጦችን ለማድረግና  ችግሮችን  ለመፍታት ነው ብለዋል፡፡ "

 በኤግዚቪሽኑ  ተሳታፊ ከሆኑት ውስጥ የአቦል ሮስተር ድርጅት ሰራተኛ  ወ/ሮ ኤልፋዝ ፍቅሩ እንደተናገረችው  በኤግዚቪሽኑ መሳተፋቸው የመጀመሪያ መሆኑን ገልፃ  እዚህ መሳተፋችን  የገዢውን ፍላጎት ለማወቅና  ራሳችንን ብሎም  የሀገራችን ምርት የሆነውን ቡና  የበለጠ  ለማስተዋወቅ  ይረዳል፡፡  እስካሁን የህብረተሰቡም  አቀባበል ጥሩ ነው ፣ መንግስትም  እያደረገልን ያለው ድጋፍ ይበረታታል በማለት አስተያይቷን ሰጥታለች፡፡

በአውደ ርዕይው 29 በምግብ ዘርፍ 33 በመጠጥ እንዲሁም 4 በፓኬጅ በድምሩ 66 የሚሆኑት ድርጅቶች  ይሳተፋሉም ተብሏል፡፡

13/08/2009