ዜና ዜና

17ኛው ታላቁ ሩጫ በኢትዮጵያ ነገ ይከናወናል

17ኛው ታላቁ ሩጫ በኢትዮጵያ ነገ በአዲስ አበባ ይከናወናል።

ታላቁ ሩጫ በዘንድሮው ውድድር ላይ ክብረወሰን የሆነ 44 ሺህ ተሳታፊዎች ሲኖሩት፥ ከ26 የዓለም ሀገራት የተውጣጡ ከ400 በላይ የውጪ ሀገር ተሳታፊዎች ተካፋይ ይሆናሉ።

ታላቁ ሩጫ ዘንድሮ በርካታ አዳዲስ አሰራሮችን ይዞ የቀረበ ነውም ተብሏል።

ከነዚህ መካከል የውድድር ሽልማት መጠኑን በእጥፍ ማሳደግ፣ የሙዚቃ ኮንሰርት ማዘጋጀት እና ተወዳዳሪዎች ያለ መወዳደሪያ ቁጥር መሳተፍ አለመቻል ዋና ዋናዎቹ ሆነዋል።

ውድድሩ መነሻ እና መድረሻውን መስቀል አደባባይ በማድረግ ነገ ጧዋት 2 ሰዓት ከ50 ደቂቃ የሚጀመር ይሆናል።

አዲስ አበባ፣ ህዳር 16፣ 2010 (ኤፍ ቢ ሲ)