ዜና ዜና

“የፍቅር እና የአንድነት ኪዳን” በሚል መሪ ቃል ሚያዝያ 7/2010 በአዲስ አበባ ሚሊኒየም አዳራሽ በተዘጋጀው ህዝባዊ መድረክ ክቡር የኢፌዴሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ አህመድ ያተላለፏቸው መልእክቶች ጥቂቶቹ፡-

= አገራችን ያለጥርጥር ታላቅ ህዝቦቿም ያለክርክር ንዑዳንና ክቡራን ናቸው፤

= መንግስት አገራዊ አንድነታችንን ለማጽናት እንደሚሰራ ደግሜ አረጋግጥላችኋለሁ፤

= ለቅሷችን የለቅሷችን መጨረሻ የሳቃችን መጀመሪያ ነው፤

= በመንግስት መዋቅር ውስጥ የሚደረገው ምደባ በችሎታና በአቅም ሆኖ ትክክለኛውን ሰው በትክክለኛ ቦታ በመመደብ አሰራራችንን እናሻሽላለን፤

= ውጤታማ ባልሆነ የተንዛዛ ስብሰባ የሚባክን ጊዜን በቀልጣፋና በዘመናዊ አሰራር ተክተን ህብረተሰቡን እናገለግላለን፤

= መጪው ምርጫ ፍትሃዊና በሁሉም ዘንድ ተአማኒ እንዲሆን፤ የሃሳብ ፍጭትም የሚደረግበት እንዲሆን ሁላችንም በቅንጅት እንደምንሰራ አረጋግጥላችኋለሁ፤

= የትምህርት ፍኖተ ካርታ ጥራትን በሚያረጋግጥ መልኩ ዳግም ይሰራል፤

= በአርሶ አደሩ እና አርብቶ አደሩ በኩል ምርትና ምርታማነትን ለማሳደግ እንሰራላን፤

= በዲፕሎማሲው መስከ በአፍሪካ ያለንን ሰላም የማስከበርም ሆነ ሌሎች ስራዎችን አጠናክረን እንቀጥላለን፤

= ሀብታም ለመሆን የተሻለው ጊዜ ወጣትነት ነው፤ ደሃ ለመሆንም ጊዜው ወጣትነት ነውና ወጣቶቻችን እባካችሁ የተሻለውን ምረጡ፤

= የዚህ ዘመን ጀግኖች ወጣቶች ናቸው፤ ወጣቶች ተስፋ ሲኖራችሁ እኛም ተስፋ ይኖረናል

= ሁላችንም ያለሁላችን ምንም ነን