ዜና ዜና

የአለም ባንክ ለኢትዮጵያ የካርበን ንግድ ፕሮጀክት የ68 ሚሊየን ዶላር ድጋፍ አደረገ

የአለም ባንክ በኢትዮጵያ ለሁለት የካርበን ንግድ ፕሮጀክቶች የሚውል የ68 ሚሊየን የአሜሪካ ዶላር ድጋፍ አደረገ፡፡

ድጋፉ ለአየር ንብረት ለውጥ መቋቋሚያ መርሃ ግብር ማስተግበሪያ በኦሮሚያ ክልል ለተመረጡ የደን ልማት ፕሮጀክቶች የሚውል ነው።

በዚህም 18 ሚሊየን የአሜሪካ ዶላሩ የተራቆተ መሬትን መልሶ ለማልማት ለሚውል ፕሮጀክት ማስፈጸሚያ ይሆናል። ቀሪው 50 ሚሊየን የአሜሪካ ዶላር ደግሞ የካርበን መጠንን ለመቀነስ ለሚደረገው ጥረት ማስፈጸሚያ ይውላል።

መርሃ ግብሩ በአካባቢው ማህበረሰብ ሊከናወኑ የሚችሉና ከደን ልማት ቱሪዝም እና ከአካባቢ ጋር ተስማሚነት ያላቸውን ስራዎች ለማስፋፋት ይውላልም ነው የተባለው።

ኢትዮጵያ በፈረንጆቹ 2025 የደን ሽፋኗን በ30 በመቶ በማሳደግ ከካርበን ጋዝ ልቀት ነጻ የመሆን ግብ አስቀምጣለች።

የአለም ባንክ መሰል ፕሮጀክቶችን በመደገፍ በሃገራት ድህነትን መቅረፍና የውጭ ቀጥታ ኢንቨስትመንት እንዲስፋፋ ስራዎችን ይሰራል።

ለአየር ንብረት ለውጥ መቋቋሚያ ቃል ከሚገባው ገንዘብ 10 በመቶ ያህሉ ብቻ ለአካባቢያዊ ፕሮጀክቶች እንደሚውል የተደረጉ ጥናቶች ያሳያሉ።

ይህም በተመሳሳይ ፕሮጀክቶች ላይ ጥርጣሬን ይፈጥራል የሚል ፍራቻን እያሳደረ ነው ሲል አፍሪካን ቢዝነስ ኢንሳይደርን ዋቢ አድርጎ የዘገበዉ ፋና ብሮድካስት ባለስልጣን ነዉ።

አዲስ አበባ ፣ መጋቢት 1 ፣ 2009 (ኤፍ ቢ ሲ)