ዜና ዜና

ኢንስቲትዮቱ 564 ቴክኖሎጂዎችንና መረጃዎችን ማቅረብ መቻሉን አስታወቀ

አዳዲስ የግብርና ቴክኖሎጂዎችንና መረጃዎችን ለተጠቃሚዎች ማቅረቡን የኢትዮጵያ ግብርና ምርምር ኢንስቲትዩት አስታወቀ ።

የኢንስቲትዩቱ የህዝብ ግንኙነት ኃላፊ አቶ ፍሰሃ ዘገየ ለዋሚኮ እንደገለጹት በ2009 ዓመት ኢንስቲትዩቱ 586 የቴክኖሎጂ መረጃዎች ለተጠቃሚዎች ለማቅረብ አቅዶ 564 ቴክኖሎጂዎችና መረጃዎችን በምርምር ማሠራጨት ችሏል ።

እንደአቶ ፍሰሃ ገለጻ ኢንስቲትዩቱ የሚያቀርባቸውን በምርምር የተገኙ አዳዲስ ቴክኖሎጂዎችን መሠረት በማድረግም በአጠቃላይ 69ሺህ 166 ለሚሆኑ የቴክኖሎጂ ተጠቃሚ አርሶ አደሮች በአዳዲስ ቴክኖሎጂዎችና መረጃዎች ላይ በሰርቶ ማሳያ የተደገፈ የክህሎት ሥልጠና ተሠጥቷል ።

ኢንስቲትዩቱ ተደራሽነቱን ይበልጥ ለማሳደግ የምርምር ውጤቱ ባለተዳረሰባቸው አካባቢዎች በሆኑት የደቡብ ፣ ሶማሌና አፋር ክልሎች የምርጥ የሰብል ዝርያዎችን ለአርሶአደሩና ለአርብቶ አደሩ ለማዳረስ ሲሰራ መቆየቱንም አቶ ፍስሃ አመልክተዋል ።

የኢትዮጵያ ግብርና ምርምር ኢንስቲትዩት ልማቱ በየደረጃው የሚፈልጋቸውን አማራጭ ቴክኖሎጂዎችን በዓይነት በብዛትና ለማቅረብ ከተለያዩ ዓለም አቀፋዊና አገር አቀፋዊ ተቋማት ጋር በጋራ እየሠራ ይገኛል ።

ነሀሴ 5/2009(ዋልታ)