ዜና ዜና

በደሴ ከተማ ለሕዳሴው ግድብ ከ4 ነጥብ 1 ሚሊዮን ብር በላይ ለማሰባሰብ ታቅዷል

በደሴ ከተማ አስተዳደር በተያዘው ዓመት ለታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ ድጋፍ የሚውል ከ4 ነጥብ 1 ሚሊዮን ብር በላይ ለመሰብሰብ ማቀዱን  የከተማው መንግሥት ኮሙዩኒኬሽን ጉዳዮች መምሪያ አስታወቀ፡፡

የህዳሴው ግድብ ችቦ ጥር 14 ቀን 2010 በደሴ ከተማ አቀባበል ይደረግለታል

የመምሪያው ኃላፊ አቶ እያሱ ዘውዱ ለኢዜአ እንደገለጹት የከተማው አስተዳደር የታላቁ ሕዳሴ ግድብ አስተባባሪ ኮሚቴ ከ4 ነጥብ 1 ሚሊዮን ብር ለመሰብሰብ የሚስችለውን የንቅናቄ እቅድ አዘጋጅቶ በመስራት ላይ ነው፡፡

እስከ መጋቢት 24 ቀን 2010ዓ.ም በሚዘልቀው ንቅናቄ  ከከተማዋ ነዋሪዎች፣ ከንግዱ ማኅበረሰብና ከመንግስት ሠራተኛው ገንዘቡን የሚሰበሰብ መሆኑን አመልክተዋል፡፡

ከዚህ በተጨማሪ በከተማ አስተዳደሩ የገጠር ቀበሌዎች በተፋሰስ ልማት የሚሳተፈው አርሶ አደር የቦንድ ግዥ እንዲፈፅሙ እንደሚደረግ  አስታውቀዋል።

ከጥር 14 ቀን 2010 ዓ.ም ጀምሮ ለሦስት ቀናት የህዳሴው ግድብ ችቦ በተለያዩ ዝግጅቶች አቀባበል የሚደረግለት ሲሆን  ስድስት ሺህ 450 ሰዎች የሚሳተፉበትም የሩጫ ውድድርም እንደሚካሄድ አመልክተዋል፡፡

በደሴ ከተማም የሕዳሴው ግድብ የድል ችቦ አደባባይ እንደሚሰየምም አቶ እያሱ አክለው ጠቁመዋል፡፡

ዝግጅቱ ከገንዘብ ማሰባሰብ ባለፈ አፍራሽ ቅስቀሳዎችን በመስበር በህዘቦች ውስጥ የእኔነት ስሜትን የሚጎለብትበት እንደሚሆንም አስታውቀዋል ብለዋል፡፡ 

በደሴ ከተማ አስተዳደር ሰራተኞች በበኩላቸው ለታላቁ ህዳሴ ግድብ ቦንድ ግዢ በመፈጸም ድጋፋቸውን እያደረጉ ሲሆን የሆኑት ወይዘሮ ዚነት አሰፋ ከዚህ ቀደም ለሕዳሴው ግድብ  በቀጣይም ግድቡ ተገንብቶ እስኪጠናቀቅ ድረስ ድጋፋቸውን እንደሚቀጥሉ አረጋግጠዋል፡፡

ባለፈው ዓመት ለታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ ከሕብረተሰቡ፣ ከነጋዴው ማኅበረሰብና ከሠራተኛው ከ1 ነጥብ 8 ሚሊዮን ብር በላይ መሰብሰቡ ይታወሳል ሲል የዘገበው የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት ነው።

ታህሳስ 27/2010፤ኢዜአ