ዜና ዜና

ጅቡቲ የነበሩ 361 ኢትዮጵያዊያን ወደ አገራቸው ተመለሱ

በጅቡቲ በስደት ላይ የነበሩ 361 ኢትዮጵያዊያን ወደ አገራቸው መግባታቸውን የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር አስታወቀ።

ስደተኞቹን ወደ አገራቸው ለመመለስ በጅቡቲ ያለው የኢትዮጵያ ኢምባሲ ከአለም አቀፉ የስደተኞች ድርጅት ጋር በተደረገው ጥረት መሆኑን ሚኒስቴሩ ለኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት በላካው መግለጫ አስታውቋል።

ስደተኞቹ ወደ አረብ አገራት ለመሄድ በህገ-ወጥ መንገድ በስደት ላይ የነበሩና የመን ውስጥ ባለው ጦርነት ምክንያት ጅቡቲ የተመለሱ ናቸው ተብሏል።

በነገው እለትም 24 ስደተኞች ወደ አገራቸው ይገባሉም ተብሏል።

አዲስ አበባ ሰኔ 5/2010 (ኢዜአ)