ዜና ዜና

በኢፌዴሪ የመንግስት ኮሙዩኒኬሽን ጉዳዮች ጽ/ቤት የተዘጋጀ ሳምንታዊ አቋም መግለጫ-የካቲት 23 ቀን 2010 ዓ.ም

የአድዋውን ድል በፀረ-ድህነት ትግሉ ልንደግመው ይገባል!

ለመላው የአገራችን ብሄር፣ ብሄረሰቦችና ህዝቦች እንኳን ለ122ኛው የአድዋ ድል በዓል በሰላም አደረሳችሁ በማለት የኢፌዴሪ መንግሥት በድጋሚ ደስታውን ለመግለጽ ይወዳል።

'አድዋ…የአብሮነትናየአንድነትተምሳሌት' በሚልመሪቃል በዛሬው ዕለት እያከበርነው ያለው የአድዋ ድል በዓል ለአሁኑ ትውልድ በርካታ ቁምነገሮችን የሚያስተላልፍ ነው።

እንደሚታወቀው፣ ጀግኖቹ አያቶቻችን አገራችንን ቅኝ ለመግዛት የፈለገ የወራሪ ሃይል በመጣባቸው ጊዜ በከፍተኛ የአገር ፍቅር ስሜትበመነሳሳት እና በላቀ የትብብር መንፈስ እንደ አንድ ሰው በመትመም በጠላታቸው ላይ የተባበረ ክንዳቸውን በማሳረፋቸውወራሪውን ሃይል መክተው መልሰዋል፤ በዚህም ከአጽናፍ እስከ አጽናፍየናኘ ታላቅ ድል አስመዝግበዋል።

ክብር ለአድዋው ጀግኖች ይሁንና፣ ዛሬ ነጻነቷ የተጠበቀች አገር የተረከበው የአሁኑ ትውልድ ደግሞ የአገሩን ነጻነትና ሉዓላዊነት በአስተማማኝ መልኩ ለማስከበር የሚቻለውበዋነኝነት የወቅቱ የህዝባችን ዋነኛ ጠላት የሆነውን ድህነት ማሸነፍ ሲቻል ብቻ መሆኑን በመገንዘብ እነሆ በፀረ-ድህነት ትግል ውስጥ ይገኛል።

በአብሮነት እና በመተሳሰብ፣ ቀደምት አያቶቻችን በክብር ያቆዩልንን አገር ወደ ከፍታ ማማ ለማውጣትየራሱን ትግል በማድረግ ላይ የሚገኘው የአሁኑ ትውልድ፣ እንደ አያቶቹ የአድዋው ገድል፣ የአብሮነታችን ምልክት የሆነውን የታላቁ ህዳሴ ግድብ እውን ለማድረግ ሌት ተቀን እየሰራ ይገኛል። በመሆኑም አድዋ የአንድነታችን አርማ እንደሆነው ሁሉ በአሁኑ ትውልድ በመገንባት ላይ ያለው የህዳሴ ግድብም የትውልዱ ህብረት፣ ቆራጥነት እና ሀገራዊ ፍቅር ምልክት ሆኖ የሚኖር ነው።

ትውልዱእስካሁን ባካሄደው የፀረ-ድህነት ትግል፣ የህዝቦቻችንን ኑሮ በመሰረቱ የለወጡ በርካታ ትላልቅ ድሎችን ማስመዝገብ ከመቻሉም በላይ ግዙፉ የድህነት ተራራ ከሥሩ የሚገረሰስበትና እንደ ጀግኖች አያቶቹ ሁሉ የራሱን ድል የሚደግምበት ጊዜ ሩቅ አለመሆኑን በተግባር ጭምር ማረጋገጥ ችሏል።

ይህም ሆኖ ግን አሁንም 22 ሚሊዮን ገደማ የሚሆነው ህዝባችን ከድህነት ወለል በታች እየኖረ በመሆኑ ትውልዱን በድሎቹ ከመኩራራት ይልቅ ለተጨማሪ ትግል መነሳሳት የሚጠይቀው ሆኗል።

በአጭሩ፣ የአገራችን ሉዓላዊነት የሚደፈረው በዋነኝነት ከፊታችን የተጋረጠውን ድህነት ሥር-ነቀል በሆነ መንገድ መፍታት ካልቻልን ነው። ከዚህ አንጻር ሲታይም የወቅቱ የሉዓላዊነት ማስከበሪያችን መንገድ የጸረ-ድህነት ትግሉ መሆኑ አያጠያይቅም።

ይህንኑ የትውልዱን ትግል ከዳር ለማድረስ መንግስት ከመቼውም ጊዜ በላቀ ሁኔታ በመንቀሳቀስ ላይ የሚገኝ ሲሆን፣ ዋነኛ አጀንዳችን የሆነውን ድህነትን የማሸነፍ እና ልማታችንን የማረጋገጥ ጥረት አሁንም በመንግስት ቅድሚያ የሚሰጠው ጉዳይ መሆኑን ለማረጋገጥ ይወዳል።

በመሆኑም ከጀግኖቹ አያቶቻችን የተረከብናት ነፃ አገር ሉዓላዊነቷ በተሟላ መልኩ ይከበርላት ዘንድ ከእነሱ የወረስነውን የአንድነትና የመተባበር መንፈስ፣ እንዲሁም ከፍተኛ የአገር ፍቅር ስሜት፣ ወኔና ጽናት ተላብሰን፣ በተጀመረው የፀረ-ድህነት ትግል የአድዋውን ድል ለመድገም ሁላችንም ልንረባረብ ይገባል።

ድህነትን ለማሸነፍ የምናደርገው ጥረት ይሳካ ዘንድም ሰላምና መረጋጋት መሠረታዊ ጉዳይ በመሆኑ ሁላችንም ሰላማችንን ለመጠበቅ ቅድሚያ ሰጥተን መንቀሳቀስ ይኖርብናል።

ያስመዘገብናቸውን ድሎች ለማስቀጠል፣ በሂደቱ የታዩብንን ድክመቶች ለማረምና ችግሮቻችንን ለመፍታትየምንችለውእንደ አድዋው ጀግኖች በከፍተኛ የአገር ፍቅር ስሜት፣ ወኔና ጽናትተባብረን ስንሰራ በመሆኑ ሁላችንም የተሻለች አገር ለመፍጠር የድርሻችንንእንድንወጣ መንግሥት ጥሪውን ያቀርባል።