ዜና ዜና

ኢትዮጵያ በፈረንጆቹ 2018 በአፍሪካ በኢንቨስትመንት መዳረሻነት አራተኛ ደረጃን እንደምትይዝ ተተነበየ

ኢትዮጵያ በፈረንጆቹ 2018 በአፍሪካ ከፍተኛ የኢንቨስትመንት መዳረሻ ከሚሆኑ ሀገራት መካከል በአራተኛ ደረጃ እንደምትቀመጥ ተተነበየ፡፡

ራንች መርቻንት ባንክ ለኢንቨስትመንት ተመራጭ ሀገራት በሚል ባወጣው ጥናት መሰረት ሀገሪቱ ፈጣን የምጣኔ ሃብት እድገት እያሳየች በመምጣቷ ተመራጭ እንድትሆን አድርጓታል፡፡

ተቋማዊ መዋቅሯ ያላትን ሃብት በሪል እስቴት፤ በትራንስፖርት እና ማኑፋክቸሪንግ ዘርፎች ላይ እንድታሰማራ እንደረዳት ባንኩ አብራርቷል፡፡

ተመጣጣኝ የሆነ የምርት እድገት ማስመዝገቧ፤ አነስተኛ የኤሌክትሪሲቲና የጉልበት ሃይል መኖር በጨርቃጨርቅ ኢንደስትሪው ላይ በተሻለ ደረጃ ለኢንቨስትመንት ተመራጭ ሆናለች ነው የተባለው፡፡

ከአፍሪካ በኢንቨስትመንት ተደራሽነት ቀዳሚ ትሆናለች ተብላ የተተነበየችው ግብፅ ስትሆን ደቡብ አፍሪካ፤ ሞሮኮ፤ ኢትዮጵያ፤ ጋና፤ ኬንያ፤ ታንዛኒያ፤ ርዋንዳ፤ ቱኒዚያ፤ ኮትዲቯር ደግሞ ከ2ኛ እስከ 10ኛ ያለውን ደረጃ ይዘዋል፡፡

ምንጭ፡ ውጭ ጉዳይ፤ ኢስትአፍሪካን ሞኒተር