ዜና ዜና

ከኢፌዴሪ የመንግሥት ኮሙዩኒኬሽን ጉዳዮች ጽ/ቤት የተሰጠ የሀዘን መግለጫ - ሀምሌ 19/2010 ዓ.ም

በታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ዋና ሥራ አስኪያጅ ኢንጅነር ስመኘው በቀለ ድንገተኛ ህልፈተ ህይወት የኢፌዴሪ መንግሥት የተሰማውን ጥልቅ ሀዘን ይገልጻል፡፡

ኢንጅነር ስመኘው በቀለ የታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ዋና ሥራ አስኪያጅ ሆነው ከተመደቡበት ጊዜ አንስቶ ለአገራቸውና ለህዝባቸው ያላቸውን ፍቅር በተግባር የገለፁ፣ የሀገርን ፍቅርን ለወገኖቻቸው በተግባር ያስተማሩ፣ ከፍተኛ መስዋእትነትን የከፈሉ፣ የዜግነትና የሙያ ግዴታቸውን በአርዓያነት የተወጡ፣ በዚህም በኢትዮጵያን ልብ ውስጥ ለዘላለም ሲታወሱ የሚኖሩ ታላቅ አገር ወዳድ፣ የልማት አርበኛ ናቸው፡፡

የኢፌዴሪ መንግሥት ለእኚህ ታላቅ ኢትዮጵያዊ አገር ወዳድ ህልፈተ ህይወት የተሰማውን ጥልቅ ሀዘን እየገለፀ፤ ለቤተሰቦቻቸውና ለመላው ኢትዮጵያውያን መጽናናትን ይመኛል፡፡