ዜና ዜና

“የአፍሪካ አማካይ ታክስ ጂዲፒ 15 በመቶ ሲሆን እኛ 12.5 በመቶ ላይ ደርሰናል”- ጠ/ሚ ኃ/ማርያም ደሳለኝ

የኢፌደሪ ጠ/ሚኒስትር አቶ ኃ/ማርያም ደሳለኝ በአምስተኛው የህዝብ ተወካዮች ም/ቤት ሁለተኛ አመት የስራ ዘመን 18ኛ መደበኛ ስብሰባ ላይ ተገኝተው የበጀት አመቱ የ6 ወራት አፈፃፀም ሪፓርት ካቀረቡ በኃላ ከህዝብ ተወካዮች ም/ቤት አባላት የመንግስት ቢሮ አሰባሰብና ታክስን በተመለከተ እየተሰራ ስላለው ስራ እና ስለመጣው ለውጥ ተጠይቀው ጠ/ሚኒስትሩ በሰጡት ምላሽ "የአፍሪካ አማካይ ታክስ ጂዲፒ 15 በመቶ ሲሆን እኛ 12.5 በመቶ ላይ ደርሰናል"ብለዋል፡፡

75 በመቶ የሚሆነውን ፋይናንስ ከሀገራዊ ገቢ ለመሸፈን ታቅዶ በ2ኛው ጂዲፒ መሰራቱን ገልፀው ታክስና ቁጠባ አሁንም በፍጥነት ማደግ እንዳለባቸው ገልጸዋል፡ ፡

የታክስ ሰብሳቢ መስሪያ ቤቶችን አቅም ማሳደግ ፣ የታክስ ህግ ማስከበርና ስርዓት ማስያዝ ላይ ጥልቅ ስራ መስራት ይጠበቅብናል ያሉት ጠ/ሚኒስትሩ የአይሲቲ ቴክኖሎጂን በመጠቀም በኩል ከደቡብ ኮርያ የተገኘውን ድጋፍ አድንቀዋል፡፡

በየአመቱ ከ10-15 በመቶ እያደገ የመጣው የሀገራችን ታክስ እድገት ለውጥ ቢያሳይም ከ20-30 በመቶ የማሳደግ ግባችን ላይ ለመድረስ ጠንክረን መስራት አለብን ጠ/ሚኒስትሩ ከዚህ ጋር በተያያዘ የውጪ አስተዳደርን በተመለከተ ሲመልሱ የዋና ኢዲተር መ/ቤትና የውስጥ ኦዲት አቅም መጠናከሩን ገልፀው የተጭበረበረ ኦዲት በሙሉ በቀጥታ ለፌደራል መርማሪ ቢሮ እንዲተላለፍ በማድረግ ወደህግ ለማቅረብና ውጤታማ ኦዲት እንዲኖር ስርዓት ተዘርግቷል ብለዋል፡ ፡