ዜና ዜና

ባለፈው ዓመት ቻይናና አፍሪካ 149 ቢሊዮን ዶላር የንግድ ልውውጥ አድርገዋል

በቻይና ዓለም አቀፍ ንግድ ማስታዋወቂያ ምክር ቤት ኃላፊ ጂያንግ ዜንግዌ የሁለትዮሽ የኢኮኖሚ ግንኙነቱን ለማሳደግ ቻይና ዋነኛ የአፍሪካ የንግድ አጋር ሆነ ትቀጥላለች ብለዋል፡፡

ጂያንግ ዜንግዌ በኢንቨስትመንት አማራጮች ላይ በቻይና ቤጂንግ በተካሄደው ስብሰባ ላይ እንደተናገሩት በቻይናና አፍሪካ መካከል ያለው የሁለትዮሽ ንግድ ልውውጡ እንደ አውሮፓዊያን አቆጣጠር በ2016 149.1 ቢሊዮን የአሜሪካ ዶላር ደርሷል፡፡

እንደ ኃላፊው ገለፃ በአፍሪካና በቻይና መካከል ያለው የንግድ ግንኙነት እየተጠናከረ በመምጣቱ የቻይና ኩባንያዎች በአህጉሪቱ በ2016 3.2 ቢሊዮን ዶላር መዋዕለ ንዋይ አፍስሰዋል፡፡

በግንባታ፣ በማምረቻ ኢንዱስትሪ፣ በአገልግሎት ሰጪ፣ በማዕድን፣ በእርሻና መሰረተ ልማቱ ዘርፍ የተሰማሩት የቻይና ባለሃብቶች ለሁለቱም አህጉሮች ልማት እና እድገት የድርሻቸውን ማበርከታቸውን ሽንዋ ዋቢ አድርጎ ኢቢሲ ዘግቧል፡፡
ሚያዚያ 13/2009