ዜና ዜና

በተያዘው የክረምት ወቅት ከ1.6 ቢሊየን በላይ የቡና ችግኝ ተተክሏል

በተያዘው የክረምት ወቅት ከ1.6 ቢሊየን በላይ የቡና ችግኝ መተከሉን የቡናና ሻይ ልማትና ግብይት ባለስልጣን አስታወቀ፡፡

በባለስልጣኑ የቡና፣ ሻይና ቅመማቅመም ልማት ኤክስቴንሽን ዳይሬክተር አቶ ብረሃኑ ጸጋዬ ለኢዜአ እንደገለጹት በተያዘው የክረምት ወቅት በ357ሺ 700 ሄክታር አዲስ መሬትና በነባር ማሳ ላይ 1.6 ቢሊየን በላይ ችግኞች ተተክሏል፡፡

ባለፉት አመታት ተተክለው ያልጸደቁ ችግኞችን መልሶ ለመተካት 305 ሚሊየን ችንግኝ መተከሉንም ጠቅሰዋል፡፡
ያረጁ የቡና ዛፎችን በመንቀል በ34 ሺ ሄክታር መሬት ላይ በአዲስ ችግኞች መተካት መቻሉም ተጠቁሟል፡፡
በየአመቱ ከሚተከሉት ችግኞች ከ70-85 በመቶ ሚሆ ነው ይጸድቃልም ብለዋል፡፡

የቡና ምርታማነትን ለማሻሻል ከጅማ የምርምር ማዕከልና ከዋና ዋና የቡና አምራች የክልል ባለሙያዎች ጋር በመሆን እየተሰራ መሆኑንም ገልፀዋል።
የአፈርና ውሃ ጥበቃ ስራዎች፣ ማዳበሪያ መጠቀም፣ በመስኖ መደገፍ፣ የጥላ ዛፎችን መትከል ፣የተሻሻሉ የቡና ዝርያዎችን ለአርሶ አደሩ ማቅረብና የቡና ማሳን ጉዝጓዝ ማልበስ ከተከናወኑት መካከል ናቸው ብለዋል።

በተያዘው የክረምት ወቅት በ423 ሺ 699 ሄክታር አዲስ ማሳ ላይ የቡና ችግኝ ለመትከል ታቅዶ እስካሁን 357ሺ 700 ሄክታር መሬት ላይ ተተክሏል።

በሀገር አቀፍ ደረጃ በሌሎች ሰብሎች እየለማ ያለውን ጨምሮ 5.4 ሚሊየን ሄክታር ቡና ማብቀል የሚችል መሬት ያለ ቢሆንም እስካሁን የለማው 1.2 ሚሊየን ሄክታር ብቻ መሆኑን ከባለስልጣኑ ያገኘነው መረጃ ያመለክታል፡፡

አዲስ አበባ ነሀሴ 6/2009 (ኢዜአ)