ዜና ዜና

ኦሮሚያ ክልል ለታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ግንባታ ከህብረተሠቡ ተሳትፎ 1 ነጥብ 7 ቢሊዮን ብር መሠብሠቡን የክልሉ ህዝባዊ ተሳትፎ ምክር ቤት ገለፀ፡፡

የህዳሴው ግድብ ግንባታ የመሠረት ድንጋይ የተቀመጠበትን 6ኛ አመት አስመልክቶ በክልል ደረጃ በሻሸመኔ ከተማ በተለያዩ ዝግጅቶች እየተከበረ ይገኛል፡፡

የክልሉ የታላቁ ህዳሴ ግድብ ህዝባዊ ተሳትፎ ምክር ቤት ጽህፈት ቤት ኃላፊ አቶ አማን አሊ በቦንድ ግዥ እና በልገሳ ከክልሉ ህብረተሠብ 1 ነጥብ 7 ቢሊዮን ብር መሠብሠብ ተችሏታል ብለዋል፡፡

በቀጣይም የክልሉ ህብረተሠብ ለግድቡ ግንባታ የሚያደርገውን ድጋፍ አጠናክሮ እንዲቀጥል ጥሪ አቅርበዋል፡፡

የሻሸመኔ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ ወይዘሮ ጠይባ ሀሰን በበኩላቸው ህብረተሠቡ ለግድቡ ግንባታ የሚያደርገው ድጋፍ ከጊዜ ወደጊዜ እያደገ መጥቷል ብለዋል፡፡

ሚያዚያ 4፣ 2009፣ኢቢሲ