ዜና ዜና

በቀጣይ ሳምንት የአለም የምግብ ቀን ለ37ኛ ጊዜ በአገራችን እንደሚከበር የእርሻና ተፈጥሮ ሀብት ሚንስትር ገለፀ ፡፡

የእርሻና ተፈጥሮ ሀብት ሚንስቴር ሚንስትር ዴታ ዳመነ ዳሮታ ዳሞታ ዛሬ ለጋዜጠኖች እንደገለጹት  በዓሉ የአለም የምግብ ቀን፣ የአለም ምግብ ፕሮግራምና የእርሻ ድርጅት  የተመሰረተበትን ቀን በማስመልከት  በየአመቱ ሲከበር ቆይቷል፡፡

በሁለተኛው የእድገትና ትራንስፎርሜሽን እቅድ  መንግስት በዋናነት ድህነትን በመቀነስ እና የምግብ ዋስትናን በማረጋገጥ በኩል በርካታ ተግባራትን እንዳከናዎነ ተጠቁሟል፡፡ 

በዓሉ በምግብ ዋስትናና በገጠር ልማት ላይ ኢንቨስት በማድረግ  የስደት ገጽታን እንቀይር  በሚል መሪ  ቃል ለ37ኛ ጊዜ  ጥቅምት  7/2010  እንደሚከበር ሚንስትሩ ተናግረዋል፡፡

የምግብ ዋስትና ማረጋገጥንና ድህነት ቅነሳን በተመለከተ በአባል ሀገራት የሚሰሩ ስራዎችን ለማሳወቅና ግንዛቤ በመፍጠር  በአሉ  ይከበራል ብለዋል፡፡

እንደሚንስትሩ ገለፃ በዓሉ በመላው አለም በአባል ሀገራት በጥቅምት ወር የመጀመሪያው ሳምንት የሚከበር ነው፡፡

በሀገር አቀፍ ደረጃ ከፍተኛ የመንግስት የስራ ኃፊዎች፣ ተቀማጭነታቸው በአዲስ አበባ የሆኑ የሌሎች ሀገራት  አምባሳደሮች ፣የአለማቀፍ ድርጅቶች ፣ከስደት ተመላሽና  ስራ ፈጣሪ ወጣቶችን በሚወክሉ  አካላት እንደሚታደሙ ይጠበቃል፡፡

ጥቅምት 2/2010 መንግስት ኮሚዩኒኬሽን ጉዳዮች ጽ/ቤት