ዜና ዜና

የኦሞ ኩራዝ ቁጥር 3 ስኳር ፋብሪካ እሁድ ይመረቃልየኦሞ ወንዝን በሚያዋስኑ በካፋና ቤንች ማጂ ዞኖች የሚገኘው የኦሞ ኩራዝ ቁጥር 3 ስኳር ፋብሪካ ከፍተኛ የመንግስት ስልጣናት በተገኙበት የፊታችን እሁድ ይመረቃል፡፡

በኦሞ ኩራዝ ስኳር ልማት ፕሮጀክት ስር ከሚገነቡት አራት ስካር ፋብሪካዎች አንዱ የሆነው ይህ ፋብሪካ ከቻይና ልማት ባንክ በተገኘ ከ8 ቢሊዮን ብር በላይ ብድር የተገነባ መሆኑን ስኳር ኮርፖሬሽን በላከልን መረጃ ገልጸል፡፡

ኮምፕላንት በተባለ የቻይና ኩባንያ የተገነባው ይህ ፋብሪካ ከ8 ሺህ እስከ 10 ሺህ ኩንታል ስኳር የማምረት አቅም ያለው ግዙፍ ፕሮጀክት ነው፡፡

***************************************
(የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት)፤ጥቅምት1/2011