ዜና ዜና

የኢ.ፌ.ዲ.ሪ ፕሬዝዳንት ዶክተር ሙላቱ ተሾመ ከቱርክ ፕሬዝዳንት ረሲፕ ኤርዶጋን ጋር ተወያዩ፡፡

ክቡር ፕሬዝዳንት ዶ/ር ሙላቱ ተሾመ በቱርክ ኢስታንቡል እየተካሄደ በሚገኘው ሁለተኛው የቱርክ- አፍሪካ የኢኮኖሚና ቢዝነስ መድረክ የመክፈቻ ስነስርዓት ላይ ንግግር አድርገዋል ፡፡

ክቡር ፕሬዝዳንቱ ፣ መድረኩ በአፍሪካና ቱርክ መካከል ያለውን የኢኮኖሚ እና የፓለቲካ ግንኙነት ወደ ላቀ ደረጃ የማሽጋገር ሚና እንደሚኖረው ገልጸዋል፡፡

በኢትዮጵያ ከ150 በላይ የሚሆኑ የቱርክ ኩባንያዎች 2 ነጥብ 5 ቢሊየን ዶላር ያህል መዕዋለንዋይ በማፍሰስ 30 ሺህ ለሚጠጉ ዜጎች የስራ እድል መፍጠራቸውን ክቡር ፕሬዝዳንት ዶ/ር ሙላቱ ተናግረዋል ፡፡

የቱርክ ኩባንያዎች በኢትዮጵያ ኢንዱስትሪ ፓርኮችና በበርካታ የቢዝነስ አማራጮች ላይ የሚያደርጉትን የኢንቨስትመንት ተሳትፎ አጠናክረው እንዲቀጥሉም ጥሪ አቅርበዋል ፡፡

ክቡር ፕሬዝዳንቱ ፣ ንግድ እና ኢንቨስትመንት የቱርክ -አፍሪካ ስልታዊ ትብብር ምሶሶዎች መሆናቸውንም አውስተዋል ፡፡

የቱርክ ፕሬዝዳንት ረሲፕ ኤርዶጋን በበኩላቸው በመድረኩ ላይ ባደረጉት ንግግር ቱርክ በአፍሪካ ያላት እንቅስቃሴ በአፍሪካ ሀገሮች ዘንድ አድናቆትን ያተረፈ መሆኑን ገልጸዋል፡፡

መድረኩ በአፍሪካ ህብረት ኮሚሽን ፣ በቱርክ የንግድ ሚኒስቴር እና የውጭ ኢኮኖሚ ግንኙነት ቦርድ ትብብር የተዘጋጀ ነው ፡፡

የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ ጽ/ቤት መስከረም 30 ቀን 2011 አ.ም