ዜና ዜና

"በሬ ለምኔ" የተሰኘው ዘመናዊ ማረሻ ወደ ስራ ሊገባ ነው

"በሬ ለምኔ" የተሰኘው ዘመናዊ ማረሻ ወደ ስራ ሊገባ መሆኑ ተገለጸ።

ቴክኖሎጂው የአርሶ አደሮችን ድካም በመቀነስ እርሻቸውን ከማቀላጠፉ በተጨማሪ ለእርሻ አገልግሎት የሚውሉ በሬዎችን በማድለብ እና ለስጋ ምርት ገበያ በማቅረብ ገቢያቸው እንዲጨምር ያግዛል ተብሏል።

የሳይንስና አቴክኖሎጂ ሚኒስቴር መረጃ እንደሚያመለክተው በኢትዮጵያውያን ባለሙያዎች ዲዛይን ተደርጎ የተሰራው እና በእጅ የሚገፋው "በሬ ለምኔ" የሚል መጠሪያ የተሰጠው ዘመናዊ ማረሻ በቅርቡ ወደ ስራ ይገባል።

የሳይንስና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር ሚኒስት ዶክተር ኢንጂነር ጌታሁን መኩሪያ የማህበረሰቡን ችግር የሚፈቱና ኑሯቸውን የሚያቃልሉ ቴክኖሎጂዎች ፈጠራና ማላመድ ላይ ሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ ትኩረት አድርጎ እየሰራ መሆኑን ተናግረዋል።

መስከረም 28፣ 2011 (ኤፍ.ቢ.ሲ)