ዜና ዜና

የኢትዮጵያ አካል ጉዳተኞች ብሔራዊ ማህበራት ፌዴሬሽን በአዲስ አበባና በአካባቢዋ በደረሰው አደጋ ማዘኑን ገለጸ

የኢትዮጵያ አካል ጉዳተኞች ብሔራዊ ማህበራት ፌዴሬሽን እና አባል ማህበራቱ ሰሞኑን በቡራዩና አካባቢዋ በተፈጸመው ጥቃት ለደረሰው የሰው ህይወት መጥፋትና ንብረት መውደም የተሰማውን ጥልቅ ሀዘን ገለጸ፡፡

ፌዴሬሽኑ ለኢዜአ በላከው መግለጫ በግጭቱ ምክንያት በጥቃቱ ለጠፋው ህይወት፣ ለደረሰው የአካል ጉዳትና መፈናቀል፣ እንዲሁም ለወደመው ንብረት የተሰማውን ሀዘን ገልጿል።

ጉዳት ከደረሰባቸው ወገኖች ጎንም በመቆም አቅም በፈቀደ መጠን አስፈላጊውን ድጋፍ እንደሚያደርግ የገለጸው ፌዴሬሽኑ፤ ድርጊቱን እንደሚያወግዝም አስታውቋል፡፡

በተፈጸመው ጥቃት ህይወታቸውን ላጡ ቤተሰቦችና ወዳጅ ዘመዶች መጽናናትን ተመኝቷል።

አዲስ አበባ መስከረም 8/2011 (ኢዜአ)