ዜና ዜና

ለህዝብ ተጠቃሚነት በኦሮሞ ህዝብ ስም የተደራጁ ፓርቲ በአንድነት መስራት ይጠበቅባቸዋል - የኦህዴድ ምክትል ሊቀመንበር አቶ ለማ መገርሳ

በኦሮሞ ህዝብ ስም የተደራጁ የተለያዩ የፓለቲካ ፓርቲዎች የተጀመረውን ለውጥ በማስቀጠል በአንድነት መስራት እንዳለባቸው የኦህዴድ ምክትል ሊቀመንበር እና የኦሮሚያ ክልል ርዕሰ መስተዳር አቶ ለማ መገርሳ አስታወቁ።

ርዕሰ መስተዳድሩ በ9ኛው የኦህዴድ ድርጅታዊ ጉባዔ የመክፈቻ ስነ ስርዓት ላይ ንግግር ባደረጉበት ወቅት በህዝቡ ስም የተደራጁ የፓለቲካ ፓርቲዎች መከፋፈል በህዝቡ አንድነት ላይ ከባድ አሉታዊ ተፅዕኖ ያለው በመሆኑ በልዩነቶቻቸው ዙሪያ በመነጋገር በአንድነት መስራት እንደሚገባችው አሳስበዋል።

የህዝብን ጥቅም በሚያስከብሩ ጉዳዮች ላይ በአንደነት መስራት እንሚያስፈልግም ገለፀዋል።

አዲስ አበባ፣ መስከረም 9፣ 2011 (ኤፍ.ቢ.ሲ)