ዜና ዜና

የሳዑዲ ዓረቢያው የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አደል አል ጁቤር ለይፋዊ የስራ ጉብኝት አዲስ አበባ ገብተዋል።

የሳዑዲ ዓረቢያው የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አደል አል ጁቤር ለይፋዊ የስራ ጉብኝት አዲስ አበባ ገብተዋል።

የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ ቦሌ ዓለም አቀፍ አየር ማረፊያ ሲደርሱ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዶክተር ወርቅነህ ገበየሁና ሌሎች የመንግስት የስራ ኃላፊዎችና ዲፕሎማቶች አቀባባል አድርገውላቸዋል።

ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አደል አል ጁቤር  ከኢፌዴሪ ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዶክተር ወርቅነህ ገበየሁ ጋር በሁለትዮሽና ቀጠናዊ ጉዳዮች ላይ ውይይት አድርገዋል፡፡

 ከጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር ዐቢይ አህመድ ጋር ተመሳሳይ ውይይት አድርገው ነገ ወደ ሀገራቸው እንደሚመለሱ   የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ አቶ መለስ ዓለም ለኢዜአ ገልጸዋል።

የኢፌዴሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር ዐቢይ አህመድ በቅርቡ በሳዑዲ ዓረቢያ ይፋዊ የስራ ጉብኝት ያደረጉ ሲሆን ጠቅላይ ሚኒስትሩ እስረኞች እንዲለቀቁ ባቀረቡት ጥያቄ መሰረት የሳዑዲ መንግስት ኢትዮጵያውያን እስረኞችን መፍታቱ ይታወሳል።

  አዲስ አበባ ነሐሴ 3/2010(ኢዜአ)