ዜና ዜና

የታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ግንባታ በኢትዮጵያ ህዝቦች ያልተቋረጠ ድጋፍ እንደቀጠለ ይገኛል፡፡

ግድቡ መላው ኢትዮጵያውያንና እና ትውልደ ኢትዮያውያን ባለቤት ሆነው እየገነቡት ያለ የኢትዮጵያ ህዝብና መንግስት ሀብት ሲሆን እስከ ሰኔ 2010 ዓ.ም 11.9 ቢሊዮን ብር ከህዝብ ድጋፍ ተሰብስቧል፡፡

በተጠናቀቀው የበጀት ዓመት ብቻ 1ነጥብ 8 ቢሊዮን ብር መሰብሰቡ ህብረተሰቡ ለግድቡ የሚያደርገው ድጋፍ እየጨመረ መሄዱን ያሳያል ፡፡
በ2010 ዓ.ም 17ሺህ 568 ያህል ዜጎች ግድቡን የጎበኙት ሲሆን ባጠቃላይ ወደ 280 ሺ ያህል ኢትዮጵያውያን እና ትውልደ ኢትዮጵያውያን በቦታው በመገኘት ግንባታውን ተመልክተዋል፡፡

ሐምሌ13/2010፤የታላቁ ህዳሴ ግድብ ህዝባዊ ተሳትፎ አ/ም/ቤት ፅ/ቤት