ዜና ዜና

የህብረተሰቡን የልማት ተጠቃሚነት የሚያሳድጉ አዳዲስ የፖሊሲ አቅጣጫዎች ተቀይሰዋል፡፡”- የኢፌዴሪ የመንግስት ኮሙዩኒኬሽን ጉዳዮች ፅህፈት ቤት ሀላፊ ሚኒስትር ክቡር አቶ አህመድ ሽዴ

የህብረተሰቡን የልማት ተጠቃሚነት የሚያሳድጉ አዳዲስ የፖሊሲ አቅጣጫዎች ተግባራዊ እየተደረጉ መሆኑን የኢፌዴሪ የመንግስት ኮሙዩኒኬሽን ጉዳዮች ፅህፈት ቤት ሀላፊ ሚኒስትር ክቡር አቶ አህመድ ሽዴ ገለፁ፡፡

ክቡር ሚኒስትሩ ዛሬ በፅህፈት ቤታቸው ጋዜጣዊ መግለጫ ሰጥተዋል፡፡

በዚሁ ጋዛጣዊ መግለጫ ወቅት እንደገለፁት አራት የመንግስት የልማት ድርጅቶች አብዛኛው ድርሻ በመንግስት ተይዞ ቀሪው ድርሻ ለአገር ውስጥና ለውጭ ባለሀብቶች በፕራይቬታይዜሽን መልክ ይተላለፋሉ ብለዋል፡፡

የድርሻ ሽግሽጉ ያስፈለገበት ዋና ምክንያት የግሉ ዘርፍ በኢኮኖሚው ውስጥ ያለውን ተሳትፎ በማሳደግ አገራዊ እድገቱን ለማፋጠን መሆኑንም ሚኒስትሩ ጨምረው ገልፀዋል፡፡

ክቡር ሚኒስትሩ አክለው እንደተናገሩት የውጭ ምንዛሬን የጥቁር ገበያ ለመቆጣጠር የሚያስችሉ ስራዎች እየተሰሩ መሆኑን ጠቅሰው ከወዳጅ አገሮችና ተቋማት በልማት ፋይናንስ መልክ የውጭ ምንዛሬን ወደ አገር ውስጥ በማስገባት ውጤታማ እንቅስቃሴዎች እየተደረጉ ነው ብለዋል፡፡

የኢፌዴሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ አህመድ ባስተላለፉት ጥሪ መሰረት በተለያየ መልኩ ተከማችተው የሚገኙ የውጭ ምንዛሬዎች ወደ ባንኮች እየገቡ በመሆኑ የባንኮች የውጭ ምንዛሬ ክምችት እያደገ መሆኑንም ሚኒስትሩ

ሐምሌ12/2010፤የኢ/መ/ኮ/ጉ/ጽ/ቤት