ዜና ዜና

“ተቋማዊ የአቅም ግንባታ ስራዎች የፅህፈት ቤቱን አገራዊ ሀላፊነት ለመወጣት ወሳኝነት አላቸው”- የኢፌዴሪ የመንግስት ኮሙዩኒኬሽን ጉዳዮች ጽህፈት ቤት ሀላፈ ሚኒስትር ክቡር አቶ አህመድ ሽዴ

የመንግስት ኮሙኒኬሽን ጉዳዮች ጽህፈት ቤት አመራሮችና ሰራተኞች በ2010 የበጀት አመት አፈፃፀምንና በ2011 ዓ.ም የበጀት አመት እቅድ ዙሪያ ዛሬ ጠዋት ውይይት አካሂደዋል።

በዚህ የውይይት መድረክ ላይ የተገኙት የጽህፈት ቤቱ ሀላፊ ሚኒስትር ክቡር አቶ አህመድ ሽዴ የተቋሙን ሁለንተናዊ አቅም መገንባት ፅህፈት ቤቱ በቀጣይ ለሚፈጽማቸው ተግባራት ወሳኝ ናቸው ብለዋል።

በህብረት መስራትና በአገር ደረጃ የተጀመረውን የለውጥ ሂደት በሚመጥን መንፈስ መንቀሳቀስ እንደሚገባም ክቡር ሚኒስትሩ የገለፁ ሲሆን ተቋሙ ለአገራዊ እድገት የበኩሉን ሀላፊነት ከመወጣት ባለፈ በኮሙኒኬሽንና ሚዲያ ዘርፍ ግንባር ቀደም ሆኖ እንዲወጣ በትጋት መስራት ያስፈልጋል በማለት አክለዋል።

በውይይት መድረኩ ላይ የ2010 የበጀት አመት ተቋማዊ አፈፃፀም ሪፖርት እንዲሁም የ2011 ዓ.ም በጀት አመት እቅድ ቀርቦ ከፅህፈት ቤቱ ሰራተኞች የተለያዩ ጥያቄዎችና አስተያየቶች የተሰጡ ሲሆን በመጨረሻም በውይይቱ በተነሱትና በሌሎች ተያያዥ ጉዳዮች ላይ በክቡር ሚኒስትሩና በሚኒስትር ዴኤታዎች ማብራሪያና አስተያየት ተሰጥቶባቸው ውይይቱ ተጠናቋል:;

ሀምሌ፣ 4/2010 የ/ኢ/መ/ኮ/ጉ/ጽ/ቤት