ዜና ዜና

በአዲስ አበባው የድጋፍ ሰልፍ በወጡ ዜጎች ላይ በተፈጸመው ጥቃት ሀዘን እንደተሰማቸው የሀይማኖት መሪዎች ገለጹ

በአዲስ አበባው የድጋፍ ሰልፍ በወጡ ዜጎች ላይ በተፈጸመው ጥቃት ሀዘን እንደተሰማቸው የሀይማኖት መሪዎች ገለጹ።

የሀይማኖት መሪዎቹ በጥቁር አንበሳ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል ተገኝተው ተጎጂዎቹን የጎበኙ ሲሆን፥ በንጹሀን ዜጎች ላይ የተፈጸመውን ድርጊት በጽኑ እንደሚያወግዙ ተናግረዋል።

ፍቅር አንድነትና ሰላም በሚሰበክበት ሰልፍ ላይ የደረሰው ጥቃት መደረግ የሌለበትና እጅግ አሳዛኝ መሆኑን ነው የሃይማኖት መሪወቹ የገለጹት።

የሀይማኖት መሪዎቹ በአደጋው ነፍሳቸውን ላጡ ዜጎች ሃዘናቸውን የገለጹ ሲሆን፥ የአካል ጉዳት የደረሰባቸው ደግሞ ከጉዳታቸው በቶሎ እንዲያገግሙ በጸሎት እንደሚያሰቧቸው ተናግረዋል።

የሃይማኖት መሪዎቹ ጉዳተኞቹ የሚያስፈልጋቸውን ድጋፍ ለማድረግም ያላቸውን ዝግጁነትም አረጋግጠዋል።

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 17፣ 2010 (ኤፍ.ቢ.ሲ)