ዜና ዜና

ጠቅላይ ሚኒስትሩ የወላይታ ሶዶና አካባቢዋን ህዝብ በማወያየት ላይ ናቸው

 

 

ጠቅላይ  ሚኒስትር ዶክተር አብይ አህመድ በወላይታ ሶዶ ከተማ ከህዝብ ጋር እየተወያዩ ነው።

ጠቅላይ ሚኒስትሩ  ሀዋሳ ተከስቶ በነበረው ግጭት ዛሬ ጠዋት በሀዋሳና አካባቢው ህዝብ ጋር ሲመክሩ ቆይተዋል።

በወላይታ ሶዶና አካባቢዋም በሀዋሳ ላይ የተከሰተውን ግጭት ተከትሎ በተነሳው ግጭት በሰው ህይወትና ንብረት ላይ ጉዳት መድረሱ የሚታወስ ሲሆን፤ ጠቅላይ ሚኒስትሩም ወደ ወላይታ ሶዶ የሄዱት በዚሁ ዙሪያ ከህዝቡ ጋር ለመወያየት  ነው።

በአሁኑ ወቅት የሶዶ ከተማና አካባቢዋ ነዋሪዎች ተወካዮች፣ የአገር ሽማግሌዎች፣ የኃይማኖት አባቶች፣ ምሁራንና በተለያየ ደረጃ የሚገኙ የመንግስት የስራ ሃላፊዎች በተገኙበት ውይይት እየተካሄደ ነው።

ጠቅላይ ሚኒስትሩ በውይይታቸው ከህዝቡ ለሚነሱት ጥያቄዎች ምላሽ እንደሚሰጡ ይጠበቃል።

 አዲስ አበባ ሰኔ 12/2010(ኢዜአ)