ዜና ዜና

ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ አሕመድ በሀዋሳ ከተማ ከህዝብ ጋር እየተወያዩ ነው።

ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ አሕመድ ለህዝባዊ ውይይት ሀዋሳ ናቸው፡፡

ጠቅላይ ሚኒስትሩ ለዚህ የህዝብ ውይይት ሲባል ትናንት ማምሻውን ሀዋሳ ገብተው አድረዋል።

በዛሬው ዕለትም ባሳለፍነው ሳምንት የፊቼ ጨምበላላ በዓል አከባበርን ተከትሎ ተከስቶ በነበረው ግጭት ዙሪያ ከህዝብ ጋር እየመከሩ ይገኛሉ።

በውይይቱም የፌዴራል ፓርላማ አባላት፣ የክልሉ፣ የሲዳማ ዞንና የሀዋሳ ከተማ የስራ ኃላፊዎች፣ የአካባቢው የሀገር ሽማግሌዎች፣ የኃይማኖት አባቶች፣ የዩኒቨርሲቲ ምሁራን እንዲሁም ከሲዳማ ዞንና ሀዋሳ ከተማ የተውጣጡ ወጣቶችና ሴቶች ይሳተፋሉ።

ባለፈው ሳምንት የፊቼ ጨምበላላ በዓል አከባበርን ተከትሎ ተከስቶ በነበረው ግጭት በሰው ህይወትና በንብረት ላይ ጉዳት መድረሱ ይታወሳል።

  ሀዋሳ ሰኔ 12/2010(ኢዜአ)