ዜና ዜና

የሞጆ የቆዳ ኢንደስትሪ መንደር በዚህ ዓመት ግንባታው እንደሚጀመር ተገለጸ

የሞጆ የቆዳ ኢንደስትሪ መንደር ግንባታ ሊጀመር ነው

በኦሮሚያ ክልል ሞጂ ከተማ የሚከናወነው የቆዳ ኢንደስትሪ መንደር ግንባታው ከ 100 ሚሊየን የአሜሪካ ዶላር በላይ ወጪ ይደረግበታል ተብሏል።

ወጪውም በኢትዮጵያ መንግስት፣ በአውሮፓ ህብረት እና ከአውሮፓ የኢንቨስትመንት ባንክ በሚገኝ ገንዘብ ነው የሚሸፈነው።

በተባበሩት መንግስታት ድርጅት የኢንዱስትሪ ልማት የአግሮ ኢንዱስትሪ ቴክኖሎጂ ዘርፍ ዋና ሀላፊ በኦርሊያ ፓትሪዠያ ካላሮባ እንደገለጹት፥ የፕሮጀክቱ አላማ ዘመናዊና ደረጃውን የጠበቀ የቆዳ ማምረቻ ኢንዱስትሪ ቀጠና መገንባት ነው።

ፕሮጀክቱ ዘመናዊ የፍሳሽ ማጣሪያ እና አወጋገድ ሰርአትን በሚያሟላ መልክ የሚገነባ መሆኑንም ነው የገለጹት።

የፕሮጀክቱ ግንባታ ሲጠናቀቅም እስከ 40 ሺህ ለሚሆኑ የአካባቢው ነዋሪዎች ስራ እንደሚፈጥር ይጠበቃል።

የሞጆ የቆዳ ኢንደስትሪ መንደር ግንባታ የዘገየውከወሰን ማስከበርና ካሳ ክፍያ ጋር በተያያዘ መሆኑ ተነግሯል።

አሁን የቆዳ ኢንደስትሪ መንደር ግንባታው በተያዘው አቅድ መሰረትም በአራት ዓመታት ውስጥ ተጠናቆ አገለግሎት መስጠት ይጀምራል ተብሎ ይጠበቃል።

 አዲስ አበባ፣ ሰኔ 5፣ 2010 (ኤፍ.ቢ.ሲ)