ዜና ዜና

ኢትዮጵያ ከኤርትራ ጋር ያላትን የድንበር ችግር በሰላማዊ መንገድ ለመፍታት ያስተላለፈቸው ጥሪ ለቀጠናው ሠላም ወሳኝ መሆኑ ተገለፀ

በጅቡቲ የኢፌዲሪ ባለሙሉስልጣን አምባሳደር ሻሜቦ ፊታሞ ከጅቡቲ የውጭ ጉዳይና የዓለም አቀፍ ትብብር ሚኒስቴር መሐሙድ አሊ ዮሴፍ ጋር በሁለትዮሽ እና አካባቢያዊ ጉዳዮች ዙሪያ ተወያይተዋል።

የኢህአዴግ ስራ አስፈፃሚ ኮሚቴ ያስተለለፈው ወሳኔ የኢኮኖሚ ማሻሻያ እርምጃዎችን የአገራችንን ኢኮኖሚያዊ እድገት ይበልጥ ለማጠናከር እንዲሁም የተሻለ የወጭ ንግድ አፈፃፀም ለማስመዝገብ መሆኑን አምባሰደር ሻሜቦ ገልፀውላቸዋል፡፡

ኢትዮ-ኤርትራ ወቅታዊ ሁኔታን በመገምገም በኢትዮጵያና ኤርትራ መካከል ተፈጥሮ የቆየው አለመግባባት እንዲያበቃና በሁለቱ ወንድማማች ህዝቦች መካከል ዘላቂ ሰላም እንዲፈጠር የኢህአዴግ ስራ አስፈፃሚ ኮሚቴ ጥሪ ማስተላለፉን ተናግረዋል።

ሚኒስትሩ በበኩላቸው ኢትዮጵያ የምታደርገው የኢኮኖሚ ማሻሻያ እርምጃዎች የኢትዮ- ጅቡቲን የኢኮኖሚ ዕድገት የሚያፋጥንና የሁለቱን አገራት ህዝቦች ተጠቀሚነት የሚያሰድግ ወቅታዊ እርምጃ መሆኑን ገልፀዋል።

ኢትዮጵያ ከኤርትራ ጋር ያለትን ችግር ለመፍታት የወሰደችው እርምጃ ተገቢና ለአፍሪካ ቀንድ ሠላም እና ልማት ጉልህ ሚና እንደሚኖረው ሚኒስትሩ ተናግረዋል።

ግንቦት 30/2010 /የውጭ ጉዳይ ቃል አቀባይ ጽ/ቤት/