ዜና ዜና

ቻይና የኢትዮጵያን የኢኮኖሚ ልማት መደገፏን እንደምትቀጥል ገለፀች

የኢፌዲሪ ፕሬዝዳንት ዶ/ር ሙላቱ ተሾመ ከቻይና ህዝባዊ ብሄራዊ ኮንግረስ ሊቀመንበርን ዛሬ አግኝተው አነጋግረዋል።

በዚህ ውይይት ላይ የቻይና ህዝባዊ ብሄራዊ ኮንግርስ ሊቀመንበር ሊ ዛንሹ ቻይና ለኢትዮጵያ የምታደርገውን ሁለንታዊ ድጋፍ አጠናክራ እንደምትቀጥል አረጋግጠዋል።

የቻይና ከፍተኛ ልዑክ የኢትየጵያ ጉብኝት የቻይና መንግስት እና የቻይና ኮሙዩኒስት ፓርቲ በኢትዮጵያ መንግስትና በገዥው ፓርቲ ኢህአዲግ መካከል ያለውን አጋርነት እንደሚያሳይ ተገልጿል።

ሊቀመንበሩ ቻይና ከኢትዮጵያ ጋር ያላትን ወዳጅነት የበለጠ ለማጠናከር ፍላጎት እንዳላትና ለሀገሪቱ የኢኮኖሚ ዕድገት ድጋፍ የምታደርግ መሆኑን ነው የገለፁት።

ሊቀመንበር ሆነው ከተመረጡ በኋላ ኢትዮጵያ በአፍሪካ የመጀመሪያ የጉብኝት መዳረሻ ማድረጋቸውም ታውቋል።

የኢፌዴሪ ፕሬዝዳንት ዶ/ር ሙላቱ ተሾመ በበኩላቸው ቻይና በሁኔታዎች የማትለወጥ ቀዳሚ የኢትዮጵያ አጋር እንደሆነችና ለሁለቱ ሀገራት ወዳጅነት ትልቅ ቦታ የምትስጥ መሆኗን ነው የገለጹት።

ሀገሪቱ ከቻይና ጋር በተለያዩ መስኮች ተባብራ ለመስራት ዝግጁ መሆኗን ነው ፕሬዚዳንት ዶክተር ሙላቱ የገለጹት።

የሁለቱ ሀገራት ግኑኙነት ከመቼውም በላይ እያደገ መምጣቱ የሀገራቱ ግንኙነት እየተጠናከረ ለመምጣቱ መሳያ ነው ብለዋል ፕሬዝዳንቱ።

ፕሬዚዳንት ዶክተር ሙላቱ በኢትዮጵያ በተካሄደው የመሰረተ ልማት ግንባታና ኢኮኖሚ እንቅሰቃሴ ቻይና ትልቅ ሚና ያላት መሆኑን ጠቅሰው ይህም ጅምር ወደፊትም ተጠናክሮ እንዲቀጥል ጥሪያቸውን አቅርበዋል።

ግንቦት 02፣2010፣(ኤፍ.ቢ.ሲ)