ዜና ዜና

ኢትዮጵያዊው አትሌት አብደላ ጎዳና የጃፓን ናጋኖ ማራቶን ውድድርን አሸነፈ

አትሌቱ ሚያዚያ 7/2010 ማለዳ በተካሄደው ውድድር ሁለት ሠዓት ከ13 ደቂቃ ከ54 ሴኮንድ በመግባት ነው ያሸነፈው።

ጃፓናዊው ዩኪ ሙናካታ በሁለት ሠዓት ከ14 ደቂቃ ከ21 ሴኮንድ ሁለተኛ ወጥቷል።

ሁለት ሠዓት ከ14 ደቂቃ ከ42 ሴኮንድ በመግባት ሶስተኛ የወጣው ጃፓናዊ ሂሮሺ ኢቺዳ የርቀቱን የግል ምርጥ ሠዓት አስመዝግቧል።

በዚህ ውድድር ከ2ኛ እስከ 10ኛ ያለውን ደረጃ የያዙት ጃፓናዊያን አትሌቶች ናቸው።

በሴቶች ውድድርም ጃፓናዊያኖቹ አትሌቶች አሳሚ ፉሩስ፣ ሳኪ ቶኮሮ እና ዩኪኮ ኦኩኖ ከ1ኛ እስከ 3ኛ ያለውን ደረጃ በመያዝ በበላይነት አጠናቀዋል።

ኬንያዊቷ ፖል ዋንጉዊ አራተኛ በመውጣት ውድድሩን አጠናቃለች።

ለ20ኛ ጊዜ የተካሄደው የናንጋኖ ማራቶን በዓለም አቀፉ አትሌቲክስ ፌዴሬሽኖች ማህበር የነሐስ ደረጃ የተሰጠው ውድድር ነው።

ኢዜአ፣ አዲስ አበባ ሚያዝያ 7/2010