ዜና ዜና

“መንግሥት ዜጎቹ የሚፈልጉትን መስማት ብቻ ሳይሆን የሚያስፈልጋቸውን ቀድሞ የማወቅና ሀገራዊ አቅም በማቀናጀት ፍላጎታቸው ደረጃ በደረጃ እውን እንዲሆን መሥራት ይሆርበታል’’-ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር አብይ አህመድ

‘'ሀገራዊ ዕድገትን ለማምጣትና እያደገ የመጣውን የሕዝብ ጥያቄ ምላሽ ለመስጠት የማስፈጸም አቅምን የሚያጎለብቱ በርካታ የለውጥ ስራዎችን ተግባራዊ ቢያደርግም በመንግሥት አካላት ዘንድ ያለው አሰራርና የህዝብ አገልጋይነት ደረጃ ወደሚጠበቀው ውጤታማነትና ቅልጥፍና አለመሸጋገሩን ያረጋገጥነው እውነታ ነው፡፡

በየዕለቱ በምትሄዱባቸው የመንግሥት አገልግሎት ሰጪ ተቋማት፣ ቀልጣፋና ፍትሐዊ አገልግሎት ባለማግኘት፣ በቅን መንፈስ የሚቀበሏችሁ ኃላፊዎችና አገልጋዮችን በማጣት መማረራችሁን እንረዳለን፡፡

በስነ ምግባር የተነፀ፣ የአገልጋይነት መንፈስ የተላበሰ ሰራተኛ እንዲኖር፣ ጉቦና የጥቅም ሽርክና፣ የዝምድናንና አድሏዊ አሰራር ጎጂ ባህል መሆኑን አውቆ ሞያውን አክብሮ፣ ለኃላፊነቱ ክብር ሰጥቶ የሚያገለግል የመንግሥት ሠራተኛና አመራር እንዲፈጠር ከመንግሥት በኩል ፅኑ ፍላጎት ያለ መሆኑን ላረጋግጥላችሁ እፈልጋለሁ፡፡ "