ዜና ዜና

አየርላንድ በኢትዮጵያ ለሰብአዊ እርዳታ የሚውል የ3 ሚሊየን ዩሮ ድጋፍ አደረገች

አየርላንድ በኢትዮጵያ ለሰብአዊ እርዳታ የሚውል የ3 ሚሊየን ዩሮ ድጋፍ አደረገች።

በአይሪሽ ኤይድ በኩል የተደረገው ድጋፍ አስቸኳይ ድጋፍ ለሚያስፈልጋቸው ዜጎች የአልሚ ምግብ፣ ንፁህ የመጠጥ ውሃ እና የመፀዳጃ አገልግሎት ለማቅረብ ይውላል ተብሏል።

አየርላንድ ከአውሮፓውያኑ 2015 ወዲህ በኢትዮጵያ ለሰብአዊ እርዳታ የሚውል ከ12 ሚሊየን ዩሮ በላይ ድጋፍ ማድረጓን በኢትዮጵያ የሀገሪቱ አምባሳደር ሶንጃ ሄላንድ ገልፀዋል።

አምባሳደር ሶንጃ ሀገራቸው ከ2014 ወዲህ በተለያዩ የትብብር ፕሮግራሞች ለኢትዮጵያ ከ130 ሚሊየን ዩሮ በላይ መስጠቷንም ነው የተናገሩት።

በቀጣይም ለተለያዩ የልማት ስራዎች እና ለሰብአዊ ድጋፍ ስራዎች ሀገራቸው ድጋፏ እንደሚቀጥል አረጋግጠዋል።

በተጨማሪም አየርላንድ ካባለፉት 25 አመታት ጀምሮ ከኢትዮጵያ ጋር በተለያዩ መስኮች በትብብር እየሰራች እንደምትገኝ አምባሳደሯ ተናግረዋል።

መጋቢት 4፣ 2010 (ኤፍ.ቢ.ሲ)