ዜና ዜና

የኢትዮጵያ እና የጣሊያን ኩባንያዎችን ያሳተፈ የንግድ ፎረምና የንግድ ለንግድ ውይይት በጣሊያን ሚላን ከተማ ተካሄደ፡፡

 

 

 

 

 

 

 

 

 

በፎረሙ ላይም ከኢትዮጵያ 20 ከጣሊያን ደግሞ 26 ኩባንያዎች ተሳትፈውበታል፡፡

ኢትዮጵያ የውጪ ባለሀብቶችን ለመሳብ መሰረተ ልማቶች እየገነባች እና የተለያዩ ማበረታቻዎችን ተግባራዊ ማድረጓን በጣሊያን የኢፌዴሪ ባለሙሉ ስልጣን አምባሳደር ወ/ሮ ዘነቡ ታደሰ ለጣሊያን ባለሀብቶች ገለፃ አድርገዋል፡

ኢትዮጵያ እየገነባቻቸው ያሉ የኢንዱስትሪ ፓርኮች የውጪ ባለሀብቶች ገብተው ቢሰሩባቸው ውጤታማ የሚሆባቸው ናቸውም ብለዋል፡፡

በኢትዮጵያ ያሉትን የኢንቨስትመንት አማራጮች በተመለከተም የኢትዮጵያ ሀገር አቀፍ የዘርፍ ማህበራት ምክር ቤት የቦርድ አባል አቶ ቢተው አለሙ ገለፃ አድርገዋል፡፡

የጣሊያን ኩባንያዎች በኢትዮጵያ ኢንቨስት ለማድረግ ከመቸውም ጊዜ በላይ የተሻለ ፍላጎት እያሳዩ መሆኑን የገለጹት የኮፊ ኢንዱስትሪያ አስ አፍሪካ ምክር ቤት ምክትል ፕሬዚዳንት ሩጌሮ አሪኮ ምክር ቤቱም ለዚህ ድጋፍ ያደርጋል ብለዋል፡፡

ከፎረሙ በተጨማሪ የኢትዮጵያ እና የጣሊያን ኩባንያዎች የንግድ ለንግድ ውይይት አድርገዋል፡፡

ፋርማሲውቲካል ግብርና ምርቶች ማቀነባበር እና ኮንስትራክሽን የተሰማሩ ኩባንያዎች በውይይቱ ከተሳተፉት መካከል ይገኙበታል፡፡ኢቢሲ የኢትዮጵያ ሀገር አቀፍ ዘርፍ ማህበራት ምክርቤት መረጃን ጠቅሶ ፅፏል።

መጋቢት3/2010