ዜና ዜና

የቱርክ ባለሃብቶች በኢትዮጵያ የሚያደርጉት የኢንቨስትመንት ተሳትፎ ይቀጥላል

የቱርክ ባለሃብቶች በኢትዮጵያ የሚያደርጉት የኢንቨስትመንት እንዲያስፋፉ የሚደረገው ጥረት ተጠናክሮ እንደሚቀጥል በኢትዮጵያ የቱርክ አምባሳደር ፌቱህ ኤሉሰይ አስታወቁ።

አምባሳደር ኤሉሶይ ለኢትዮጵያ ከፍተኛ ዲፕሎማቶችና የፓርላማ አባላት እየተሰጠ ባለ ስልጠና ላይ እንደገለጹት የአገራቸው ባለሃብቶች በኢትዮጵዩ ያላቸውን የንግድና ኢንቨስትመንት ተሳትፎ አንዲያሳድጉ ታበረታታለች ብለዋል።

በአሁኑ ወቅት ከሁለት ቢሊዮን ዶላር በላይ ያስመዘገቡ የቱርክ ባለሃብቶች በኢትዮጵያ በተለያዩ የኢንቨስትመንት ዘርፎች ተሰማርተው እንደሚገኙ ገልፀዋል። በዚህም ለ30 ሺህ ኢትዮጵያውያን የስራ እድል ፈጥረዋል።

ሁለቱ አገራት ያላቸውን ታሪካዊ ግንኙነት በመጠቀም የንግድና ኢኮኖሚ ትስስራቸውን የበለጠ ለማሳደግ መስራት እንዳለባቸውም ገልፀዋል።

ለሶስት ቀናት በሚቆየው ስልጠና ከቱርክ የዲፕሎማሲ አካዳሚ በመጡ ከፍተኛ ዲፕሎማቶች በአለም ዓቀፍ ግንኙነትና ተዛማጅ ጉዳዮች ስልጠና እየተሰጠ ነው።

አካዳሚው ካሁን ቀደም ለ13 ኢትዮጵያውያን ዲፕሎማቶች ስልጠና መስጠቱ

መጋቢት4/2010/የዉ/ጉ/ሚንስቴር