ዜና ዜና

የጃፓን ባለሀብቶች በፋርማሲቲካል ዘርፍ ለመሰማራት ፍላጎት እንዳለቸው ተገለጸ

የጃፓን ባለሀብቶች ከኢትዮጵያውያን ባለሀብቶች ጋር በመተባበር በፋርማሲቲካል ዘርፍ በተለይም በቆዳና የአይን እንክብካቤ ጤና ዘርፍ ላይ ለመሰማራት ማሰባቸውን በኢፌዲሪ ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር የቢዝነስ ማስፋፊያ ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር አቶ አርአያ ገብረእግዚያብሔር ገለጹ ፡፡

ዳይሬክተሩ እንዳሉት የጃፓን የቢዝነስ ተወካዮች ከውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዴኤታ ከዶክተር አክሊሉ ጋር ባደረጉት ውይይት በኢትዮጵያ ባለው ሰፊ የኢንቨስትመንት አማራጮች መሳባቸውንና አገራቸው የካበተ ልምድ ባገኘችበት የፋርማሲቲካል ዘርፍ ለመሰማራት መስማማታቸውን ጠቅሰዋል፡፡ ምንም እንኳ የኢንቨስትመንት መጠኑ በውል ያልታወቀ ቢሆንም ጃፓን በፋርማሲቲካል ዘርፍ ትልቅ ልምድ እና አቅም ስላላት በአይነትም ሆነ በመጠን ከፍ ያለ ኢንቨስትመንት ልታደርግ እንደምችል ጠቁመዋል፡፡

የጃፓን የቢዝነስ ተወካዮች በአገሪቱ የተለያዩ ቦታዎች በተለይም በቂሊንጦ የኢንዱስትሪ ፓርክ የሚገኘው ፍርማሲቲካል ዘርፍን እንደሚጎበኙ እና ከተለያዩ ሚኒስትር መስሪያ ቤቶችም ጋር በተለያዩ ጉዳዮች የልምድ ልውውጥ እንደሚያደርጉ ታውቋል፡፡

መጋቢት4/2010/አዲስ ዘመን