ዜና ዜና

የደቡብ ወሎ ዞን ነዋሪዎች ለህዳሴው ግድብ የ6 ሚሊዮን ብር የቦንድ ግዢ ፈጸሙ፡፡

የደሴ ከተማ ከንቲባ አቶ ላቀው ከበደ በጋራ ባለቤትነት የተጀመረው ታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ኢትዮጵያዊ አንድነት ይበልጥ እንዲጎላ የሚያደርግ መሆኑን ተናግረዋል፡፡

ከኦሮሞ ብሄረሰብ አስተዳደር ዞን በቃሉ ወረዳ ሃርቡ ከተማ የህዳሴ ግድብ የድል ችቦውን የተረከበው ደቡብ ወሎ ዞን ለደሴ ከተማ አስረክቧዋል፡፡

የደሴ ከተማ ከንቲባ አቶ ላቀው ከበደ ችቦው የኢትዮጵያ ህዝቦች ለጋራ ዕድገት መስራታቸውን አጉልቶ የሚያሳይ ነው ብለዋል፡፡
የደቡብ ወሎ ዞን ነዋሪዎች ችቦው መምጣቱን ተከትሎ የ6 ሚሊዮን ብር የቦንድ ግዢ አድርገዋል፡፡

ከዞኑ መንግስት ኮሚኒኬሽን የተላከው መረጃ እንደሚያመለክተው ከግድቡ ጅምር አንስቶ የዞኑ ህዝብ ከ172 ሚሊዮን ብር በላይ በቀጥታና በቦንድ ግዢ እንዲሁም በተፈጥሮ ሀብት ልማት ስራም 6 ሚሊዮን ብር የሚገመት የጉልበት ድጋፍ አድርጓል፡፡

የዞኑ ነዋሪዎች በቀጣይም ለግድቡ ግንባታ ድጋፋቸውን አጠናክረው እንደሚቀጥሉም ተናግረዋል፡፡

ኢ.ቢ.ሲ