ዜና ዜና

አርብቶ አደሮች ለድርቅ ተጋላጭ እንዳይሆኑ የተሰሩ ሥራዎች ውጤት እያመጡ መሆኑ ተገለፀ

በኢትዮጵያ አርብቶ አደሩና ከፊል አርብቶ አደሮች ለድርቅ ተጋላጭ እንዳይሆኑ የተሰሩ ሥራዎች ውጤት እያመጡ መሆኑ ተገለፀ፡፡

ይህ የተገለፀው የእንስሳትና ዓሣ ሀብት ሚነስቴር የድርቅ መቋቋሚያና አርብቶ አደር ኑሮ ማሻሻያ ፕሮግራም አፈፃፀም ግምገማ በድሬዳዋ ባካሄደበት ወቅት ነው፡፡

ኢትዮጵያ የድርቅ ተጋላጭትን ለመቋቋም ለ5 ዓመታት የሚቆይ መርሐ ግብር ቀርፃ ተግባራዊ ማድረግ ጀምራች፡፡

ፕሮጀክቱ ከዓለም ባንክ ጋር በመተባበር በ49 ሚሊዮን ዶላር በአፋርና ኢትዮጵያ ሶማሌ ክልል በሚገኙ 15 ወረዳዎች ላይ እየተተገበረ ይገኛል፡፡

በዚህም በተደጋጋሚ በተፈጥሮና ሰው ሰራሽ ምክንያቶች አርብቶ አደሩ ላይ ይደርሱ የነበሩ የድርቅና የጎርፍ አደጋዎች መቀነሳቸው በመድረኩ ተገልጿል፡

የውኃ አጠቃቀም፣የመኖና ሌሎች ሥራዎችም በአርብቶ አደሩና ከፊል አርብቶ አደሩ አካባቢዎች በስፋት ይከናወናሉ ተብሏል፡፡

ኢቢሲጥር 3፡2010