ዜና ዜና

የአማራ ክልል ምክር ቤት መደበኛ ጉባኤውን ማካሄድ ጀመረ

የአማራ ክልል ምክር ቤት 5ኛ ዙር 3ኛ ዓመት የስራ ዘመን 8ኛ መደበኛ ጉባኤ ተጀምሯል፡፡

የምክር ቤቱ አፈጉባኤ አቶ ይርሳው ታምሬ በመክፈቻ ንግግራቸው እንዳሉት፥ የህዝቡ የፍትሐዊ ተጠቃሚነት ጥያቄ ምላሽ እንዲያገኝ ምክር ቤቶች አሰራሮችን በመፈተሸ ተገቢ መፍትሄዎችን መፈለግ እና ጥብቅ ቁጥጥር ማድረግ አለባቸው ብለዋል።

በመሆኑም የህዝብ እንደራሴ የሆኑት ምክር ቤቶች ሃላፊነታቸውን መወጣት ይገባቸዋል ነው ያሉት።

ጉባኤው የአማራ ክልል ትምህርት ቢሮ፣ የአማራ ብዙሃን መገናኛ ድርጅት እና የአካባቢ ጥበቃ አፈጻጸምና የጣና ጉዳይ ላይ እንደሚወያይ ይጠበቃል።

በመጨረሻም በተለያየ ደረጃ ያሉ የዳኞችን ሹመት እንደሚያፀድቅ ተነግሯል።፡፡

ምንጭ፦የአማራ ብዙሃን መገናኛ ድርጅት

አዲስ አበባ፣ ህዳር 16፣ 2010 (ኤፍ ቢ ሲ)