ዜና ዜና

ኢትዮጵያ ከለጋሽ ሃገራት የምታገኘውን ገንዘብ በአግባቡ እንደምትጠቀምበት ተገለጸ

ኢትዮጵያ ከለጋሽ ሀገራት በምታገኘው የገንዘብ ድጋፍ መሰረታዊ አገልግሎቶችን ተደራሽ እያደረገች መሆኑን የገንዘብና ኢኮኖሚ ትብብር ሚኒስቴር ገለፀ፡፡

የገንዘብ ድጋፉ ለታለመለት አላማ ስለመዋሉ የሚገመግም ውይይት በአዲስ አበባ ተካሂዷል፡፡

ባለፈው አመት ከለጋሽ ሀገራት በተገኘ ገንዘብ በመላ ሃገሪቱ የተከናወኑ የመሰረታዊ አገልግሎቶች ሪፖርት ቀርቧል፡፡

በዚህም ኢትዮጵያ የምእተ አመቱን የልማት ግቦች ልታሳካ የቻለችው እነዚህ መሰረታዊ አገልግሎቶች በአግባቡ በመከናወናቸው ነው ተብሏል፡፡

ለዘንድሮ በጀት አመትም አለም ባንክ ለዚሁ መርሀ ግብር ማስፈፀሚያ የሚውል የ6መቶ ሚሊዮን ዶላር የገንዘብ ድጋፍ አድርጓል፡፡

ህዳር 5/2010/ኢቢሲ/