ዜና ዜና

ኢትዮጵያና ኳታር በተለያዩ ጉዳዮች ላይ ስምምነት ተፈራረሙ፡፡

ጠቅላይ ሚኒስትር ኃይለማርያም ደሳለኝ ከኳታር አሚር ሼክ ታሚም ቢን ሃማድ አል ታኒ ጋር ተወያዩ።

በጠቅላይ ሚኒስትር ኃይለማርያም የሚመራው ከፍተኛ ልዑክ ለይፋዊ የስራ ጉብኝት ትናንት ኳታር መዲና ዶሃ መግባቱ ይታወቃል።

የኳታሩ አሚር ሼክ ታሚም ቢን ሃማድ አል ታኒ ዛሬ በቤተ መንግስታቸው ለጠቅላይ ሚኒስትር ኃይለማርያም ደሳለኝ አቀባበል አድርገውላቸዋል።

ጠቅላይ ሚኒስትር ኃይለማርያምና አሚር ታሚም ቢን ሃማድ የሁለቱ አገሮች ግንኙነት በሚጠናከሩ ጉዳዮች ዙሪያ ተወያይተዋል።

ሁለቱ አገሮች ግንኙነታቸውን ወደ ላቀ ደረጃ ለማድረስ በሚያስችሉ የዲፕሎማቶች ቪዛ አሰጣጥና የኢንቨስትመንት ጥበቃ ጉዳዮች ላይ ስምምነት ተፈራርመዋል።

የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዶክተር ወርቅነህ ገበየሁ ከኳታር አቻቸው ሞሓመድ ቢን አብዱልራህማን አልታኒ ጋር በዲፕሎማቶች ቪዛ አሰጣጥ ዙሪያ ስምምነት ተፈራርመዋል።

የገንዘብና ኢኮኖሚ ትብብር ሚኒስትር ዶክተር አብረሃም ተከስተ ከኳታር የኢኮኖሚና ንግድ ሚኒስትር አህመድ ቢን ጃሲም አልታኒ ጋር የኢንቨስትተመንት ጥበቃ ስምምነቱን ተፈራርመዋል።

  ዶሃ ህዳር 5/2010(ኢዜአ)