ዜና ዜና

አለም ዓቀፍ የአበባ አውደ ርዕይ በኔዘርላንድ በመካሄድ ላይ ይገኛል፡፡

ኢትዮጵያ በኔዘርላንድ አገር ውስጥ በመካሄድ ላይ በሚገኘው ስምንተኛው ዓለም አቀፍ የአበባ የንግድ ትርኢት ላይ በንቃት በመሳተፍ ላይ ትገኛለች፡፡

በየጊዜው በጥራትና በዓይነት ለአለም ገበያ በማቅረብ ላይ የምትገኘውን ልዩ ልዩ አበባዎችን ከተለያዩ ሀገራት ለመጡ ገዢዎችና ለኢንቨስተሮች በማሳየት ላይ ትገኛለች፡፡

በንግድ ትርዒቱ ላይ ሀገራችንን በመወከል የኢትዮጵያ ሆርቲካልቸር አምራችና ላኪዎች ማህበር ጨምሮ በዘርፉ በሀገራችን የተሰማሩ ባለሀብቶች ምርቶቻቸውን በማሳየት ላይ ይገኛሉ፡፡

በንግድ ትርዒቱ ኢትዮጵያን ጨምሮ ከ23 አገራት የተውጣጡ 262 አምራች ላኪዎችና በመሳተፍ ላይ እንደሚገኙ በብራሰልስ የሚገኘው የኢትዩጵያ ኤምባሲ በላከልን መረጃ ለመረዳት ችለናል፡፡

ኤምባሲውም ጨምሮ በአሁኑ ወቅት ኔዘርላንድ በሀገራችንን ጋር በንግድና ኢንቨስትመንት ረገድ ያላት የኢኮኖሚ ግንኙነት ከአውሮፓ ሀገራት በግንባር ቀደምትነት ላይ የምትገኝ መሆኑን ገልጾ ግንኙነቱ በላቀ የእትራቴጂክ ፓርትነርሽፕ ደረጃ ላይ የሚገኝ መሆኑን ገልጿል፡፡

መንግስታችን በዘርፉ እየተመዘገበ ያለው እድገት ለመደገፍ እያሳየ ያለው ቁርጠኛ አቋም፣ በዘርፉ ውስጥ የተሰማሩት ባለሀብቶች እያሳዩ ካሉት ብርቱ ጥረት የተነሳ እንደሆነ መገንዘብ ይቻላል፡፡

በአሁኑ ወቅት በዘርፉ በኢትዮጵያ ውስጥ ያለው የኢንቨስትመንት ሁኔታ ሳቢ እየሆነ መምጣቱን ተሳታፊዎቹ የገለፁ ሲሆን፣ በዘርፉ የሚያጋጥሙ ተግዳሮቶች ለመፍታት መንግስት በሁተኛው ሀገራዊ የልማትና ትራንስፎርሜሽን እቅድ አፈፃፀም የበለጠ ተጠቃሚ የሚያደርገን ስራዎችን በማከናወን ላይ ይገኛል፡፡

ሀገራችን በዘርፉ ያለውን አጠቃላይ አላስፈላጊ ቢሮክራሲ መቀነስ ብትችልና የምርቶቹ ልዩነቶች ያገናዘበ የማቀዝቀዣ መሳሪያዎች በካርጎዎች ውስጥ ቢተከል ሳይበላሹ ከዘርፉ የሚገኘውን ገቢ ከፍ ማድረግ እንደሚቻል ተሳታፊዎቹ ገልጸዋል፡፡

ህዳር 4/2010 /በባልቲክና አውሮፓ ህብረት ሀገራት የኢፌዲሪ ኤምባሲ/