ዜና ዜና

ግብይቱን ከግብርናዉ ዘርፍ ጋር በማስትሳሰር አምራቹን ተጠቃሚ ለማድረግ እየተሰራ ነዉ፡፡

በምእራብ ጎጃም ዞን የተለያዩ ወረዳዎች የሚገኙ አርሶ አደሮች በዘመናዊ መንገድ የታገዘ ግብርና በመከተላቸዉ የተሻለ  ተጠቀሚ መሆናቸዉን  ገለፁ፡፡

ወጣቶች በማህብር በመደራጀት  የአርሶ አደሩን ምርት በመቀበል እሴት ጨምርዉ ለገበያ ቢያቀርቡም የተለያዩ ችግሮቻቸዉ እዳልተፈቱላቸዉ በአካባቢዉ ጉብኝት ላደረጉት ከፍትኛ የመንግስት የስራ ሀላፊዎች ገልፀዋል፡፡

የገበያ ትስስር ችግር   እና የብድር አቅርቦት አለማግኝታቸዉ ወጣቶቹ ካነሱዋቸዉ ጥያቄዎች በጥቂቱ ናቸዉ፡፡

በንግድ ሚኒሰቴር የንግድ ማስፋፊያ ዘርፍ ሚኒስትር ዴኤታ አቶ አያና ዘዉዱ  በአገር ውስጥ ግብይት ስርአቱ  ያሉ ማነቆዎችን በማስወገድ  የኤክስፖርት አቅምን ለማሳደግ እየተሰራ መሆኑን አብራርተዋል፡፡

በአገር ዉስጥ የገበያ ክፍተት እንዳይፈጥር አምራቹን  ከገዢ ጋር የሚያገናኙ አዉደ ርእዮችን በመጠቀም ርስብርስ ማሰተዋወቅ አስፈላጊ ነዉ ብለዋል፡፡

ሌላዉ በማህበር የተደራጁ አምራቾች ቀጥታ ከላኪ ባለሀብቱ ጋር የሚገናኝበት አስራር ሊመቻች ይገባል፡፡

እንደ ሚኒስተሩ ገለፃ  በበጀት አመቱ ከግብርናዉ ዘርፍ 4 ቢሊየን ዶላር የዉጭ ምንዛሬ ለማግኘት እቅድ ተይዟል፡፡

ለዚህም በአገር ደረጃ ብሄራዊ ኤክስፖርት ካዉንስል ተቋቋሞ ወደ ስራ ገብቷል፡፡

የገበያ ችግርን ለመፍታት ምርትን ገበያዉ ከሚፈልግዉ ጥራትና መጠን ከማምርት ባለፈ አንዳንድ ምርቶች ላይ ብራንድ ማዉጣት አስፈላጊ መሆኑን አብራርተዋል፡፡

ወጣት አስማማዉ ወርቁ በምእራብ ጎጃም ዞን መርአዊ ከተማ የተባበር የወተት ማቀነባበሪያ ማህበር ስራ አስኪያጅ ነዉ፡፡

በአካባቢዉ የወተት አቅርቦቱ ከፍላጎታቸዉ በላይ በመሆኑ በማህበር ከተደራጁ አቅራቢዎች ብቻ እንድሚረከቡ ገልጷል፡፡

በቀን ከ6000 ሊትር ወተት በላይ እንደሚረከቡ ይገልፃል ሆኖም ወደ ትልልቅ ከተሞች ለመድረስ የተሽከርካሪ እጥረት እንዳለባችዉ  ተናግሯል፡፡

ይህን ችግር ለመፍታት የብድር አቅርቦት እንድምቻችላቸዉ ጥያቄ አቅርቧል፡፡

ጥቅምት 08/2010