ዜና ዜና

በአዲስ አበባ የጤና ተቋማት ማስፋፊያ እየተደረገላቸው ነው፡፡ዶ/ር አሚር አማን

በአዲስ አበባ ከተማ  የጤና ተቋማት ማስፋፊያ እየተደረገላቸው መሆኑን የጤና ጥበቃ ሚንስትር ዴኤታ ዶ/ር   አሚር አማን ገለጹ፡፡

ማስፋፊያ እየተደረገላቸው የሚገኙት የጤና  ተቋማትም በሚዲያ  ባለሞያዎች  ተጎብኝተዋል ፡፡

በአዲስ አበባ ከተማ ውስጥ ከሚገኙት ሆስፒታሎች  የጥሩነሽ ቤጅንግ ሆስፒታል ፣ የቅዱስ ጴጥሮስ ቲቪ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል እና በኦሮሚያ ክልል  የጫንጮ የመጀመሪያ ደረጃ ሆስፒታል የማስፋፊያ ፕሮጀክቶቹ  ተጎብኝተዋል፡፡

የጤና ጥበቃ ሚንስቴር ሚንስትር ዴታ  ዶር አሚር  አማን እንደገለፁት የጤና ተቋማቱን  ፕሮጀክት  ማስፋፊያ መደረጉ  በዋናነት የህብረተሰቡን የመልካም አስተዳደር ጥያቄ  ለመፍታት ያለመ ነው ብለዋል፡፡

ለአብነትም ያህል የቅዱስ ጳውሎስ ሆስፒታል በፊት ከነበረበት 170 የበሽተኛ አልጋዎች  በአሁኑ ስአት  በእናቶችና ህፃናት ብቻ  ከ300 በላይ  የሚይዙ አልጋዎች ተጠናቆ   ወደስራ ይገባል ተብሏል፡፡በ 1 ቢሊየን ብር  ተጨማሪ ስፔሻላይዝ ያደረገ የካንሰር ፣የልብና ሌሎችንም   የህክምና ባለሞያዎች  መኖሪያዎችም  በመገንባት ህክምና ለመሰጠት እየተሰራ መሆኑም ታውቋል፡፡

የጥሩነሽ ቤጅንግ ሆስፒታል በበኩሉ  የማስፋፊያ ፕሮጀክት  እያካሄደ ሲሆን ዘመናዊ የህክምና መሳሪያዎችና  የባለሙያዎች መኖሪያም እንዲሁ ከማስፋፊያ ፕሮጀክቶች ውስጥ ተካተዋል፡፡

በ2010 በአዲስ አበባ ከተማ እንዲሁ 3 ትልልቅ ሆስፒታሎች  እንደሚገነቡም የጤና ጥበቃ ሚንስትር መረጃ ያመላክታል፡፡

ጥቅምት 2/2010 የመንግስት ኮሚዩኒኬሽን ጉዳዮች ጽ/ቤት