ዜና ዜና

በሚቀጥሉት አመታት መንግስት ለባቡር መስመርና ለመንገድ መሰረተ ልማቶች የበለጠ ትኩረት ሰጥቶ ይሰራል ፣- ዶ/ር ሙላቱ ተሾመ

የኢ.ፌ.ዴሪ ፕሬዝዳንት ዶክተር ሙላቱ ተሾመ 5ኛውን የህዝብ ተወካዮች እና የፌዴሬሽን ም/ቤቶች 3ኛ አመት የስራ ዘመን የጋራ ስብሰባ የመክፈቻ ስነ-ስርአት ላይ ተገኝተው እንደተናገሩት በሚቀጥሉት አመታት መንግስት የጀመራቸውን የመሰረተ ልማት ስራዎች አጠናክሮ ይቀጥላል፡፡

በ2009 ዓ.ም በገጠር ትራንስፎርሜሽን ትልቁን ሚና የሚጫወተውን የገጠር መንገድ ተደራሽነት ለማረጋገጥ በተሰራው ስራ 75 በመቶ ያህል የገጠር ቀበሌዎች እርስ በእርስ እንዲገናኙ መደረጋቸውን አውሰተዋል፡፡

እንደ ፕሬዝዳንቱ ገለጻ የተጀመረውን የገጠር ቀበሌዎችን በመንገድ ኔትወርክ የማገናኘት ስራ ወደ 85 በመቶ ለማድረስና በሚቀጥሉት ሁለት አመታትም ሁሉንም የገጠር ቀበሌዎች ለማዳረስም እየተሰራ ነው፡፡

ፕሬዝደንቱ በሪፖርታቸው አክለው እንደገለፁት በቅርቡ ግንባታው የተጠናቀቀው የአዲስ አበባ ጅቡቲ የባቡር መስመር የተሟላ አገልግሎት እንደሚሰጥና ሌሎች በግንባታ ሂደት ላይ ያሉትንም ፕሮጀክቶች ስራ ተጠናክሮ ይቀጥላል፡፡
የመንግስት ኮሚዩኒኬሽን ጉዳዮች ጽ/ቤት መስከረም 30/2010 ዓ.ም